መለጠፊያ ውይይት:የኢራን ባህል ማዕከል - ኢትዩጵያ
- እስላሚክ ሪፐብሊክ ኢራን ወይም (جمهوری اسلامی ایران /ጆምሁሪ-የ ኢስላሚ-የ ኢራን)1,648,195 ኪ.ሜ2 ስፋትና 81,000,000 የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት። በሰሜኑ ወይና ደጋ የአየር ንብረት ውስጥ በስተደቡብ ስፍራ ላይ፣በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ፣ከ250 00’ እስከ 390 47 ሰሜናዊ ላቲቲዩድ እና ከ440 02’ እስከ 630 20’ ግሪንዊች መካከል
ኢራን ከቱርክሚንስታን፣ አዘርባጃን ና አርሜንያ ጋር በስተሰሜን በኩል፤ ከአፍጋኒስታንና ፓኪስታን ጋር ደግሞ በስተምስራቅ እንዲሁም ከኢራቅና ቱርክ ጋር ደግሞ በምዕራብ በኩል ትዋሰናለች። የአለማችን ትልቁ ሀይቅ የሆነው የካስፒያን ባህር ከኢራን በስተሰሜን ሲገኝ፤የፐርሽያ ሰላጤ (ከኦማን ባህር ትይዩ) ደግሞ ከኢራን በስተደቡብ ይገኛል።
የኢራን ኢስላማዊ ሬፑብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: مهر خاوران | ||||||
ዋና ከተማ | ቴህራን | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፋርስኛ | |||||
መንግሥት {{{መሪ ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
ዓሊ ኽሃመነኢ ሓስሳን ሮኡሃኒ ዐስሃቅ ጃሃንጊሪ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,648,195 (17ኛ) 0.7 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት |
82,800,000 (18ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ፋርስ ሪኣል ﷼ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +3:30 | |||||
የስልክ መግቢያ | +98 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .ir ایران. |
የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚንስትር በቅርቡ በ2010 ባወጣው መረጃ መሰረት ኢራን 31 ግዛቶችና 387 ከተማ ቀመስ ሥፍራዎች አሏት። እያንዳንዱ ግዛት የተለያዩ ከተማ ቀመስና ወረዳዎች አሉት። በወረዳ ውስጥ ከተሞችና መንደሮች ትንሾቹ ቦታዎች ናቸው።ኢራን በተለያዩ መልክአ ምድራዊ ምክንያቶች አራት አይነት ወቅቶች ያላት ሀገር ናት ለእነዚህ የተለያዩ መልክአ ምድራዊ ገፅታዎቿ ከአውሮፓ፣ ከሜድትራንያን ባህር፣ ከአፍሪካ የሰሀራ በርሃ፣ ከህንድ ውቅያኖስ፣ ከኢስያ ውስጣዊ ከፍተኛ ስፍራዎች እና ከቀዝቃዛ የአየር ፀባይ አካባቢ አጠገብ መገኘቷ አንዱ ምክንያት ነው። በተጨማሪም ሰፊ ቦታ፣ የበዙ ተራሮችና የበረሃ ስፍራዎች እንዲሁም በሀገሪቱ በስተደቡብና በስተሰሜን በኩል ሁለት ትላልቅ ባህሮች መኖራቸው ኢራን የተለያዩ አይነት የአየር ፀባያት እንዲኖራት አስችሏታል።
እነዚህ የተለያዩ የአየር ፀባያት በሦስት ሊከፈሉ ይችላሉ። እነዚህም ደረቅና ከፊል ደረቅ፣ ቀዝቃዛ ተራራና የወይን አደጋ ተራራ እና ካስፒያን ናቸው። “ኢራን” የሚለው ቃል አርያኖች ወደ ከፍተኛው ስፍራ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከቦታው ታሪክ እኩል የቆየ ስያሜ ነው። በመካከለኛው የፐርሽያ ቋንቋ ስያሜው ‹ኤራን› የሚል የነበረ ሲሆን ይህም ‹አርያናም› ከሚለው ከጥንቱ የኢራኖች ቋንቋ የተገኘ ነው። እንደ ተወሰኑ አጥኚዎች እምነት “አርያን” የሚለው ስያሜ (በጥንቱ እንዲካ አርያ፣ በጥንቱ ኢራንያን አርያ፣ በጥንቱ ፐርሽያ አርያ እና በአቬስተን ኢሪአ) ትርጉም “ምርጥ” ማለት ነው።
የዚህን አካባቢ ታሪክ በግሪክና ላቲን ፅሑፎች ውስጥ በምንፈልግበት ጊዜ የምናገኘው ኢራን ከሚለው ቃል ይልቅ ከግሪኩ “ፔርሲአ” ከሚለው ቃል የመጡትን “ፔርስ” ወይም “ፔርሱን” የሚሉትን ቃላት ነው። ከ1935 (እ.አ.አ) ጀምሮ ግን ሀገሪቱ በአለም አቀፍ መድረክ “ኢራን” ተብላ መጠራት ጀመረች። ጥንታዊው የኢራን ምድር በአሁኑ ሰአት 31 ግዛቶች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱም የራሱ የሆነ የተለያዩ ታሪካዊ፣ መልከዓምድራዊና ባህላዊ ገፅታዎች ያሉት ቢሆንም ህዝቡ ግን አንድና የተዋሀደ ነው። በብሄራዊው የ2006 የህዝብ ቆጠራ መሰረት በእነዚህ 31 ግዛቶች ውስጥ ከ81,000,000 የሚበልጥ ህዝብ አለ ሴት 51በመቶ፣ ወንድ 43 በመቶ ናቸው የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ “ሪያል” ነው። የሀገሪቱ ብሄራዊ ሀይማኖት እስልምና ሲሆን አብዛኞቹ ሰዎች ሙስሊሞች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ግን የራሳቸው የሆነ በዓላትና ሀይማኖትዊ ክንውኖችን በነፃነት የሚያከብሩ አናሳ የሆኑ የክርስትና፣ የአይሁድና የዞሮስቴሪያን እምነት ተከታዮችም አሉ። የዚህ ምድር ነዋሪዎች ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ መንግስታት ወጥተው ወርደዋል። በሜድያን፣ በአካሜንድ፣ በፐርቲያንና በሳሳኒድ የአስተዳደር ጊዜያት ኢራን የአለም ልእለ-ሀያል ሀገር ሆና ነበር። በመጨረሻም ብዙ ባህልና ስልጣኔ ያላቸው ህዝብ ሆነው ወደ እስልምና ሀይማኖት ገብተዋል።
እነ ሳማኒድ፣ ክዋርዝሚድ፣ ሳፋቪድ፣ አፍሻሪድ፣ ዘንድ እና ቃጃር ስርወ-መንግስታት በነበሩበት ባለፈቱ 15 መቶ ክፍለ ዘመናት ውስጥ በፍልስፍናውና በሳይንሱ ረገድ ድንቅ የሆነ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር። በእነዚህ ዘመናት ውስጥ ኢራናውያን ለሀገራቸው ደማቸውን አፍሰዋል፤ በሀገሪቱን እድገት፣ ሀይማኖታዊነት እና ክብር ላይ ያነጣጠረን አደጋ ሁሉ መክተዋል። በኢራን የተደረገው የእስልምና አብዮት ህዝቡ ከከፈላቸው መስዋእቶች መካከል የቅርቡ ጊዜው ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል።
በ1960ዎቹ የተቀጣጠለው የእስልምና አብዮት ኢማም ኾሜይኒ በፌብሩዋሪ 1, 1979 ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በድል ተጠናቋል። በአስር ቀናት ውስጥ ብቻ (ማለትም በፌብሩዋሪ 11 ,1979) አብዮቱ ተጠናቀቀ። በኤፕሪል 1, 1979 በተደረገው ሪፈረንደም መሰረት 98.2 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ደግፎትና መርጦት የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ተቋቋመ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዚች ጥንታዊ ምድር በኢማም ኾሜይኒ መሪነትና በአያቶላህ አሊ ኻሜኒኻ ተተኪነት አዲስ ዘመን ተበሰረ። የገዢዎቹ ተቀዳሚ አላማዎች የሚባሉት ገለልተኛነት፣ ነፃነት፣ የወሰን መከበር እና የኢራንን እስላማዊነት መጠበቅ ናቸው። ለ8 አመታት በዘለቀው በኢራቅ የጦርነት ጊዜያት እንኳን የህዝቡ ቀናኤነት ለአፍታ እንኳ አልተፈታም ነበር። በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ኢራን ጥሩ ደረጃዎችን በማለፍ ብሩህ ተስፋ ወዳለው ጊዜ በመገስገስ ላይ ትገኛለች።