መርዝ ሐረግ
Appearance
መርዝ ሐረግ (Toxicodendron radicans፤ እንግሊዝኛ፦ Poison Ivy) በምሥራቅ ካናዳና በአሜሪካ አገራት፣ እንዲሁም በጃፓን፣ ምሥራቅ ቻይናና ሩስያ በፓሲፊክ ውቅያኖስ አጠገብ፣ በብዛት የሚበቅል የዱር ዕጅግ አስቸጋሪ አረም ነው።
ይህ ዝርያ ምንም ጥቅም የለውም። ቅጠሎቹ በመርዛም ዘይት ተሸፍነዋል፣ ይህም ዘይት በአብዛኛው ሰዎች ቆዳ ላይ ሃይለኛ እከክና ሽፍታ ያደርጋል።
የሚታወቀው በሦስት ቅጠሊቶቹ አብረው በራሳቸው አገዳ ላይ ነው። እሾሕ የለውም። በመፀው ወራት ቅጠሎቹ ቀይ ይሆናሉ።
ልጆች በተለይ የአረሙን መታወቂያ ባለማወቃቸው ወደ ዱር ሔደው ሲመለሱ በሽፍታ ይሸፈናሉ።
ሽፍታው በጥቂት ሰአት ውስጥ በሳሙናና በውሃ ካልታጠበ፣ ፈሳሽ ቁስል ሊሆን ይችላል። የቁስሉ ፈሳሽ ግን እከኩን አያስፋፋም። ብዙ ደቂቃ ሳያልፍ በደንብ ቢታጠብ ቁስል አይሆንም። ያም ሆነ ይህ ቁስሉ በጣም መጥፎ ቢሆንም በሁለት ሳምንት ያህል ይድናል።