Jump to content

ሞቃዲሾ

ከውክፔዲያ
(ከመቋዲሾ የተዛወረ)

ሞቃዲሾ (ሶማልኛ፦ Muqdisho ሙቅዲሾ) የሶማሊያ ዋና ከተማ ነው።

ሞቃዲሾ በ 1992

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,208,800 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 02°02′ ሰሜን ኬክሮስ እና 45°21′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በ50 ዓም ገደማ በግሪክኛ በተጻፈው «የቀይ ባሕር ጉዞ» ዘንድ፣ ከ«በርበሮች» ነጻ ከተሞች (በሶማሊያ ስሜን ዳር) በኋላ፣ ከሶማሊያ ምዕራብ ዳር ጀምሮ እስከ አሁን ሞዛምቢክ ድረስ ያለው ጠረፍ ወይም «አዛኒያ» ለሒምያር (የመን) ንጉሥ ካሪብ ኢል ተገዥ ነበር። በዚህም ጊዜ «የሳራፒዮን ፈሳሽ» ይጠቅሳል፣ ይህም የሞቃዲሾ ሥፍራ (ዋቢ ሸበሌ ወንዝ አፍ) እንደ ነበር ይታስባል።

ሞቃዲሾ ከ686 ዓ.ም. ጀምሮ ታውቆአል። በዚያን ጊዜ ሡልጣን አብዱል ማሊክ ቢን ሙሪያሚ እንደራሴውን እንደሾመበት ይባላል። የወደቡም መጀመርያ ስም «ሐማር» ተባለ። ከመካከለኛ ዘመን በናዲር ብዙ መሐለቅ ከቻይና በመገኘቱ፣ ከሩቅ አገሮች ንግድ እንደ ተደረገ ይመሰክራል። የዛንዚባር ሡልጣን በ1863 ዓ.ም. ከተማውን ያዙ። እሳቸው በ1884 ዓ.ም. ለጣልያኖች አከራዩት። በ1897 ዓ.ም. ጣልያኖች በሙሉ ገዙትና የጣልያ ሶማሊያ መቀመጫ ሆነ። የእንግሊዝ ሃያላት ከጣልያ በ2ኛ አለማዊ ጦርነት1933 ዓ.ም. ያዙት። በኅዳር ወር 1942 ዓ.ም. ጣልያኖች እንዲመልሱ ተፈቀደ። በ1952 ዓ.ም. ሶማሊያ ነጻ አገር በሆነበት ወቅት ሞቃዲሾ የአገሩ ዋና ከተማ ሆነ።