Jump to content

ሚካያ በሀይሉ

ከውክፔዲያ
ሚካያ በሀይሉ
ሚካያ በሀይሉ በአልበሟ ሽፋን ላይ
መረጃ
የልደት ቀን ግንቦት ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም.
ያረፉበት ቀን ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.

ሚካያ በሀይሉ (ከግንቦት ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነበረች።

የህይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሚካያ ከእናቷ ከወይዘሮ ሙሉ እመቤት ፀጋዬ እና ከአባቷ አቶ በሀይሉ ገለታ ግንቦት ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ ተወልዳ ያደገች ስትሆን ከአምስት ልጆች የመጀመሪያ ናት።[1][2] የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በቤተልሄም 1ኛ ደረጃ የህዝብ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በአብዮት ቅርስ ት/ቤት ተከታትላለች።[1] ሚካያ ግጥም መድረስ የጀመረችው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለች ነበረ።

በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ ድንገት በኢቲቪ የአለቤ ሾው ቀርባ ስታዜም የተመለከቷት የሙዚቃ አቀናባሪ አልያስ መልካና ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ወዲያው የአብረን እንስራ ጥያቄ አቀረቡላት።[1] ካልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ የመጀመሪያ አልበሟን በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. ሸማመተው በሚል መጠሪያ ለመልቀቅ በቅታለች።[1][2]

አርቲስት ሚካያ ከአገር ውስጥ ድምፃውያን አስቴር አወቀ እና አለም ከበደ፣ ከአገር ውጭ ደግሞ ቶኒ ብራክስተን እና ትሬሲ ቻፕማን እንደ ምሳሌ ትጠቅሳለች።[2]

ሚካያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ የመጀመሪያ ድግሪዋን አግኝታለች።[1] ከሙዚቃ ስራዋ ውጭ በመምህርነት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሰራች ሲሆን የሁለተኛ ድግሪዋን በመከታተል ላይ ነበረች።[1] በተጨማሪም ዓላማው ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ መጎልበት የሆነ «ሚካያ አርት ወርክስ» የተሰኘ ድርጅት አቋቁማለች።[1]

ሚካያ በገጠማት የደም ስር መቆጣት የህክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በድንገት ህይወቷ አልፏል።[1] የቀብር ስነ ስርዓቷ በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ተፈፅሟል።[1] ሚካያ በሀይሉ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነበረች።[1]

የስራዎች ዝርዝር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ደለለኝ(ግጥም)

ደለለኝ(6) ማሬ ነሽ ብሎ አታለለኝ

ወተቴ እያለ ሸነገለኝ

ቅቤ ምላስህ ደለለኝ ደለለኝ

....Edit by Yoseph Endale (yosephendale154@gmail.com)[3]

  1. ^ ኢሬቴድየአርቲስት ሚካያ በሀይሉ ቀብር ስነ ስርአት ተፈፀመ
  2. ^ አርቲስት ሚካያ በሀይሉ ከአለባቸው ተካ ጋር በአለቤ ሾው ያደረገችው ቃለ መጠይቅ
  3. ^ yosephendalewereta@gmail.com