Jump to content

ማህፈድ

ከውክፔዲያ

ሳተርን፡ (ምልክት፦♄) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 6ኛ ( ስድስተኛ ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪቬነስመሬትማርስ እና ጁፒተር የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ኡራኑስነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።

ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሁለተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተርኡራኑስነፕቲዩን እና ራሱ ሳተርን ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን ከተባለ ጋዝ እና በ ጥቂት መጠን ሂሊየም ከተባለ ንጥረነገር የተሰራ ነው።

ፕላኔቱ በተለይም ዙሪያውን በሚገኙ በቀለበቶቹ ይታወቃል። እነዚህ ቀለበቶች ከሳተርን ወገብ ከ6630 ኪ.ሜ. እስከ 120700 ኪ.ሜ. ርቀት ድረስ ይገኛሉ። በአማካይ እያንዳንዳቸው እስከ 20 ሜ. ድረስ ወፍረት ያላቸው ቀለበቶች ናቸው። የተሰሩት በአብዛሃኛው ከውሃ፣ ከበረዶ እና ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ነው።