ማላቦ

ከውክፔዲያ
ማላቦ

ማላቦ (Malabo) የኢኳቶሪያል ጊኔ ዋና ከተማ ነው።

የማላቦ አቀማመጥ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 100,000-150,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 03°45′ ሰሜን ኬክሮስ እና 08°48′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ በቢዮኮ ደሴት (ቀድሞ 'ፌርናንዶ ፖ') ላይ ይገኛል።

ከተማ የተመሠረተው በእንግሊዞች ደሴቱን ከእስፓንያ ሲከራዩ በ1819 ዓ.ም. ነበር። በዚያን ጊዜ ስሙ 'ፖርት ክላሬንስ' (Port Clarence) ነበረ። የባርያ ፈንጋዮች ንግድ ለማቆም ተመሠረተ። አንዳንድ ነጻ የወጣ ባርያ ደግሞ እከተማው ሠፈረ። በኋላ ከነዚህ ሠፈረኞች ብዙ ወደ ሴየራ ሌዎን ቢፈልሱም የሌሎች ክፍል ልጆች እስከ ዛሬ በማላቦ ተገኝተው ቋንቋቸው የፖርቱጊዝ-አፍሪካዊ ክሬዮል አይነት ነው።

የኪራይ ጊዜ አልቆ ደሴቱ ወደ እስፓንያ ሲመለስ የከተማው ስም 'ሳንታ ኢዛቤል' (Santa Isabel) ሆነ። በ1961 ዓ.ም. የኤኳቶሪአል ጊኔ ዋና ከተማ ወዲህ ከባታ ተዛወረ። በ1965 ስሙ 'ማላቦ' ሆነ።