ማይክሮሶፍት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ኢንዱስትሪ ኮምፒዩተር ሶፍትዌር
ኮምፒዩተር ሐርድዌር
ቴሌቪዥን
ምርምርና ማዳበር
ኢንተርኔት
ገቢ $44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.)
ቅርንጫፎች {{{ድህረገፅ}}}


ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን ዓለም-አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። እንደ ጁላይ 2006 እ.ኤ.አ. ማይክሮሶፍት 71,553 ሠራተኞች በ102 ሀገሮች ሲኖረው፣ ዓመታዊ ገቢው 44.28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነው። እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማምረትና ማዳበር ዋና ዓላማው ነው። ዋና መስሪያቤቱ በሬድመንድ፣ ዋሽንግተንአሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ታዋቂ ምርቶቹ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ስርአተ ክወና እና ማይክርሶፍት ኦፊስ ግሴት ሶፍትዌር ያጠቃልላሉ። ከሶፍትዌሮች ሌላ፥ ኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ የኬብል ቴሌቪዥን፥ ኤም.ኤስ.ኤን. ዌብሳይትማይክሮሶፍት ኢንካርታ የኢንተርኔት መዝገበ ዕውቀት፥ የቤት መዝናኛ እና ሌሎችም ምርቶችና አገልግሎቶችን ያቀርባል።