ቢል ጌትስ

ከውክፔዲያ

ዊሊያም ሄንሪ ቢል ጌትስ IIIአሜሪካ እ.አ.አ. ኦክቶበር 28 1958 የተወለደ ታዋቂ የቢዝነስ ሰው እና የማይክሮሶፍት የሶፍትዌር አምራች ድርጅት መስራችና ባለቤት ነው። ድርጅቱን የመሰረተው ከፖል አለን ጋር በመሆን በ አፕሪል 4 1975 እ.ኤ.አ. ኒው ሜክሲኮ ውስጥ ነበር። ግለሰቡ እ.አ.አ. ከ1995 - 2010 ድረስ (2007ን ሳይጨምር) የአለማችን ከበርቴ ሰው ነው። በአሁኑ ጊዜ የማይክሮሶፍት ሊቀመንበር እና ስፔሺያል ሶፍትዌር አርኪቴክት ነው። ጌትስ በዘመናዊው የኮምፒውተር እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረገ ግለሰብ ነው።