ምዕራፍ

የምዕራፍ ጨረሩ (በአረንጓዴ የሚታየው) አንድ ቁስ ከማነጻጸሪያ ነጥብ ያለውን ርቀትና አቅጣጫ የሚለካ ነው። በአብዛኛው ጊዜ ይዚህ ጨረር መጠን ቁሱ ከተጓዘው ርቀት ያንሳል። በሌላ አነጋገር የአረንጓዴው ቀስት ርዝመት ከሰማያዊው ያንሳል (ሰማያዊው ርቀት ነው)።
ምዕራፍ ከአንድ መነሻ ነጥብ ተንስቶ መድረሻ ነጥብ ላይ የሚደርስ ከሁሉ መስመር በላይ በጣም አጭሩ ርቀት ነው። ስለሆነም ምዕራፍ፣ ምናባዊ ቀጥተኛ መንገድ ነው። የምዕራፍ ጨረር የዚያን ቀጥተኛ መስመር ርዝመትና አቅጣጫ ይወክላል። ብዙ ጊዜ ይህ ጽንስ ሃሳብ በተፈጥሮ ኅግጋት ጥናት ዘርፍ ተጠቃሚነትን ያገኛል። ፍጥነት፣ ፍጥንጥነትን ለማስላት ይህ ጽንሰ ሃሳብ አይነተኛ መሳሪያ ነው።