Jump to content

ሞፕሶስ

ከውክፔዲያ

ሞፕሶስ በጥንታዊ ግሪክኛ አፈታሪክ የሚገኝ ስም ነው። በዲዮዶሮስ ሲኩሉስ ዘንድ በድሮው ዘመን በሊኩርጉስ (የጥራክያ ንጉሥ) መንግሥት ውስጥ ሞፕሶስ አለቃ ሲሆን ሊኩርጉስ በቅያሜ ከጥራክያ አባረረው። ያንጊዜ ደግሞ የእስኩቴስ አለቃ ሲፑሉስን አባረረው። ከጊዜ በኋላ ግን የአማዞኖች ሥራዊት ንግሥት ሚሪናሊብያ አንሥታ በእስያ (ሶርያና ታናሹ እስያ) ዘምታ ወደ አውሮፓ ተሻገረችና ጥራክያን ወረረች። በዚያን ጊዜ ሞፕሶስና ሲፑሉስ ከስደት ተመልሰው ከነወገኖቻቸው አማዞኖቹን በውግያ አሸነፉዋቸው፤ ሚሪናም ተገደለች። የቀሩት አማዞኖች አውሮፓን ትተው ሞፕሱስና ሲፑሉስ ተከተሉዋቸውና እስከ ሶርያ ድረስ አገሩን አቀኑ። በአንዳንድ ምንጭ ሞፕሱስ (ወይም ደግሞ ሞክሱስ) በኪልቅያ ሥርወ መንግሥት መሠረተ።

በሌላ አፈ ታሪክ ዘንድ ሞፕሱስ ንግርተኛ ሆኖ ከአርጎናውቶች ጋር ወደ ኮልቂስ (የዛሬው ጂዮርጂያ) በጀብዱ ሄደ። ወደ ግሪክ አገር ሳይመለሱ በሊብያ ከሜዱሳ ጋራ ሲታገሉ ሞፕሶስ በእፉኝት ተነከሰና ሞተ።