ሊኩርጉስ (የጥራክያ ንጉሥ)

ከውክፔዲያ

ሊኩርጉስ (ሉኮርጎስ) በግሪክ አፈታሪክ የጥራክያ ንጉሥ ነበር። ከትሮያን ጦርነት አስቀድሞ እንደ ገዛ በብዙ ጽሐፊዎች ከነሆሜር ተጽፎዋል።

ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ እንደሚለን፣ ይህ ሊኩርጉስ አምባ ገነን ሆኖ ከአለቆቹ አንድ ሞፕሶስ የተባለውን ከመንግሥቱ አባረረው። በተጨማሪ የእስኩቴስን ሰው ሲፑሉስን አባረረው። ከዚህ ጥቂት ጊዜ በኋላ ግን አማዞኖች የተባሉት ሴት ወታደሮች ከሊብያ አንስተው አገሩን ወረሩ። ያንጊዜ ሞፕሶስና ሲፑሉስ ከስደት ተመልሰው ሠራዊታቸው ከአማዞኖች ጋር በተዋገው ውግያ ንግሥታቸው ሚሪና ተገደለችና ተሸነፉ።

በኋላ ዘመን ግን አፒስ ዲዮኔሶስ በየአገሩ ስለ ግብርና እያስተማረ ተዛውሮ ከእስያ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲፈልግ ሊኩርጉስ ግን አቃወመው። ኦሲሪስ ግን ሊኩርጉስን ገደለውና በፈንታው አለቃውን ማሮን አገረ ገዥ አደረገው።