ሢንኃይ አብዮት

ከውክፔዲያ
የቻይና ሥራዊት በማንቹዎች ላይ ሲነሡ፣ ናንኪንግ፣ ሢንኃይ አብዮት፣ 1904 ዓም

ሢንኃይ አብዮት1904 ዓ.ም. በቻይና አገር ጪንግ መንግሥት ላይ የተከሠተ አብዮት ነበረ።

የቻይና ጪንግ መንግሥት1636 ዓም ጀምሮ በማንቹ ብሔር ከባድ ገዥነት ሥር ሆኖ ነበር። ሆኖም ማንቹዎቹ ከቻይና ብሔሮች በሕዝብ ብዛት ጥቂቶች ነበሩ። ከዚህም በላይ ከ1636 ጀምሮ ለቻይናዊ ወንድ ሁሉ ጉንጉን (የቻይና) ጽጉር ይገደድ ነበር።

ባለፉት አመታት፣ የጪንግ ማንቹዎች ከቻይና ሕዝብ መሬት መካከል አያሌ ርስቶች ለውጭ አገር ድርጅቶች ይሼጡ ጀመር። ከዚህም ጋር ብዙ ተራ ሕዝቦች ከመሬታቸው አስለቅቀው መዛወር ተገደደባቸው።

ለጪንግ መንግሥት ብዙ ተቀራኒ ስብስቦች በምስጢር በቻይና ሕዝብ መካከል ተነሡ። የነዚህ ስብስቦች ማህበር ወይም «ቶንግመንግኊ መሪ ሱን ያት ሰንአሜሪካ ወይም አውሮፓ ይቆዩ ነበር። በመጀመርያ ለአመታት አብዮቶቻቸው ሁሉ አልተከናወኑም ነበር። በ1904 ዓም ግን በዉቻንግ ከተማ በሆነው ሁከት ሠራዊቱ ከነአለቆቻቸው ጋር ለአብዮት እርዳታቸውን ሰጡ። ከዚህ በኋላ አብዮት ወደየከተማውና ወደየክፍላገር ቶሎ ተስፋፋና በአዲስ ሪፐብሊክ ተባበሩ። በዚያን ጊዜ በዙፋን ላይ የተቀመጠው ጪንግ ንጉሥ ሕፃን ልጅ ስለ ነበር፣ በሚከተለው ዓመት ዙፋኑን ተወና መላው ቻይና ሪፐብሊክ ሆነ። ነገር ግን ኃይለኛ የሆነው የቀድሞ ጪንግ ሥራዊት አለቃ ይዋን ሽካይ ስለ ነበር በዶ/ር ሱን ፋንታ እርሱ የቻይና መሪ በኋላም ለአጭር ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ሆነ።