Jump to content

ሪቻርድ ፓንክኸርስት

ከውክፔዲያ
(ከሪቻርድ ፐንኸርስት የተዛወረ)
ሪቻርድ ፓንክኽርስት

ዶክተር ሪቻርድ ፐንክኸርስት ዲሴምበር 3፣ 1927 እ.ኤ.አ. ከእንግሊዛዊቷ እናታቸው ሲልቪያ ፓንክኸርስትና ጣሊያናዊ አባታቸው ሲልቮ ኮሮ ተወለዱ። በባንክሮፍት'ስ ስኩል ኢን ውድፎርድ (en: Bancroft's School in Woodford) ቀዳሚ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ (en: London School of Economics) የኢኮኖሚካዊ ታሪክ ዶክትሬት አግኙ [1] [2]

የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሪቻርድ ፓንክኸርስት እናት ወይዘሮ ሲልቪያ ፓንክኸርስት ከሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጀምረው የኢትዮጵያ ባህልና ነጻነት ደጋፊ እንደነበሩ በሰፊው ይተረካል። ስለሆነም ህጻኑ ሪቻርድ ብዙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በማወቅ አደጉ። በስተመጨረሻ፣ ሲልቪያ ፓንከኸርስት Ethiopia, a Cultural History የሚለውን መጽሐፋቸውን በ1955 እ.ኤ.አ.) ካሳተሙ በኋላ ልጃችተውን ሪቻርድን ይዘው በሚቀጥለው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ጠቅለለው ሄዱ። ቀጥሎም ሪቻርድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ጀመረው በ1962 የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል መስራች ዲሬክተር ለመሆን በቁ። .[1] ከዚህ ጊዜ ጀመሮ Journal of Ethiopian Studies እና Ethiopia Observer የተባሉትን መጽሔቶች ዋና አዘጋጅ ሆኑ[1]

ከአብዮቱ መነሳት በኋላ፣ በ1976 ሪቻርድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለቀው ወደ እንግሊዝ አገር ተሰደዱ። በዚያውም የ en:School of Oriental and African Studies እና en:London School of Economics ጥናት ጓድ ከሆኑ በኋላ የen:Royal Asiatic Society ቤተ መጻሕፍተኛ ሆኑ[2]። በ1986 እ.ኤ.አ.፣ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በስደት አቋርጠውት የነበረውን የኢትዮጵያ ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጠሉ .[1]

በፋሺስት ወረራ ጊዜ በሙሶሊኒ ትዕዛዝ ከኢትዮጵያ በዘረፋ ተወስዶ በሮማ ከተማ ላይ ቆሞ የነበረውን የአክሱም ሐውልት ወደ ኢትዮጵያ ለማስመልስ የሚደረገውን ጥረት በመምራት 2008 እ.ኤ.አ. ሐውልቱ ወደአክሱም ተመልሶ እንዲተከል አድርገዋል[1]። ለኢትዮጵያ ጥናት ባደረጉት ጥረት የen:Officer of the Order of the British Empireን ማዕረግ በen:Queen's Birthday Honours ተሸልመዋል[3] ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በዙ መጻሕፍትን በመድረስ ይታወቃሉ።

ፕሮፌሰር ፓንክኸርስት፣ ባጠቃላይ 400 ጽሑፎችን ለዓለም አቀፍ መጽሔቶች ሲያቀርቡ፣ 22 መጽሓፎችን በትብብር እና 17 መጽሓፎችን በራሳቸው ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ትውፊት ደርሰዋል።

  1. ^ Indrias Getachew, Dr. Richard Pankhurst — Historian, Race and History
  2. ^ Close and Personal: Interview with Dr. Richard Pankhurst, Senamirmir
  3. ^ LondonGazette፣12 June 2004