ራሆተፕ

ከውክፔዲያ
ሰኸምሬዋኻው ራሆተፕ
ራሆተፕ መስዋዕት ለጣኦት ሲሰጥ
ራሆተፕ መስዋዕት ለጣኦት ሲሰጥ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1588-1584 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 2 ደዱሞስ ?
ተከታይ 1 ሶበከምሳፍ
ሥርወ-መንግሥት 17ኛው ሥርወ መንግሥት


ሰኸምሬዋኻው ራሆተፕላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1588-1584 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ የሚታወቅ በተለይ ከሁለት ጽላቶች ሲሆን የጤቤስና የቆፕቶስና የአቢዶስ ቤተ መቅደሶች እንዳሳደሰ ይዘግባሉ። በብዙ ዘመናዊ ሊቃውንት አስተሳሰብ ይህ የሆነ የሂክሶስ ወገን ከስሜን ወርረው ስላጠፋቸው ይሆናል። ስለዚህ ሂክሶስ ወደ ስሜን ተመልሰው ይህ ራሆተፕ የ17ናው ሥርወ መንግሥት መስራች ይቆጥሩታል። ይህ ግን ተከራካሪ ነው፤ ሌሎች በሌላ ሥርወ መንግሥት ነበር የሚሉ አሉ።

ቀዳሚው
2 ደዱሞስ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1588-1584 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ሶበከምሳፍ