2 ደዱሞስ

ከውክፔዲያ
ጀድነፈሬ 2 ደዱሞስ
የጀድነፈሬ ደዱሞስ ጽላት
የጀድነፈሬ ደዱሞስ ጽላት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1591-1590 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 4 ሰኑስረት ?
ተከታይ ራሆተፕ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት


ጀድነፈሬ 2 ደዱሞስላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1591-1590 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ የሚታወቅ ከአንድ ጽላትና «ጀድነፈሬ» ከሚል ጥንዚዛ እንቁ ነው። በዚያ ጽላት ከሂክሶስ ጋራ ጦርነት እንዳደረገ ይጠቅሳል።

ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ ከሰኸምሬ ሸድዋሰት ቀጥሎ አምስት የፈርዖን ስሞች ጠፍተዋል። በአቶ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ ጀድነፈሬ በነዚህ አምስት መካከል ነበሩ። ቅደም-ተከተላቸው ግን አይታወቅም።

ፍላቪዩስ ዮሴፉስ ዘንድ ማኔቶንን ሲጠቅስ ሂክሶስ የገቡት በፈርዖን «ቱቲማዮስ» ዘመን ሲሆን ከዚያ ሂክሶስ ከሥልጣን አወረዱት ይላል። በአንድ አስተሳስብ የ«ቱቲማዮስ» መታወቂያ 2 ደዱሞስ ነው። ያም ሆነ ይህ የሂክሶስ ፈርዖን አፐፒ ከ1590 እስከ1588 ዓክልበ. ድረስ ጤቤስን እንደ ያዘና 16ኛውን ሥርወ መንግሥት እንዳስጨረሰ ይታመናል። ከ2 አመት በኋላ በ1588 ዓክልበ. አዲስ ግብጻዊ ፈርዖን ራሆተፕ ተነሥቶ የ17ኛው ሥርወ መንግሥት መስራች ይባላል።


ቀዳሚው
4 ሰኑስረት
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1591-1590 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ራሆተፕ