1 ሶበከምሳፍ
Appearance
==
| ሰኸምሬዋጅኻው ሶበከምሳፍ | |
|---|---|
| የ1 ሶበከምሳፍ ሐውልት | |
| የግብጽ ፈርዖን | |
| ግዛት | 1584-1577 ዓክልበ. ግ. |
| ቀዳሚ | ራሆተፕ ? |
| ተከታይ | 2 ሶበከምሳፍ |
| ባለቤት | ኑበምሃት |
| ሥርወ-መንግሥት | 17ኛው ሥርወ መንግሥት |
==

ሰኸምሬዋጅኻው ሶበከምሳፍ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1584-1577 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ የሚታወቅ በተለያዩ ጽላቶችና ሐውልቶች ነው። ጉዞዎች ወደ ዋዲ ሐመመት ድንጋይ መፍለጫ ይላክ እንደ ነበር ይታወቃል። አንዱ ጽሑፍ ከ7ኛው አመት ሲሆን ዘመኑ ቢያንስ 7 ዓመት እንደ ቀረ ሊታወቅ ይችላል። እንዲሁም ንግሥቱ ኑበምሃት፣ ሴት ልጁ ሶበከምኸብ፣ እና ወንድ ልጁ ተከታዩ 2 ሶበከምሳፍ ይታወቃሉ።

| ቀዳሚው ራሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1584-1577 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 2 ሶበከምሳፍ |