ሰመንካሬ ነብኑኒ

ከውክፔዲያ
ሰመንካሬ ነብኑኒ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1800-1798 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 6 አመነምሃት
ተከታይ ሰኸተፒብሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ሰመንካሬ ነብኑኒ (ወይም ነብኑንነብነኑ) ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1800 እስከ 1798 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የ6 አመነምሃት ተከታይ ነበረ።

ሕልውናው ከአንድ ጽላት ብቻ ተረጋግጧል። ይህም ጽላት በሲና ልሳነ ምድርኩልእርሳስ ማዕድን ቦታ ተገኘ። በኋላ ዘመን በተጻፈው በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ ሲጠቀስ የዘመኑ ርዝመት ግን በከፊል ከሰነዱ ጠፍቶ ስለ ሆነ፣ «ነብኑኒ <..> እና ፳፪ ቀን ገዛ» ብቻ ሊነብ ይቻላል። የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት ለ፪ ዓመታት ብቻ ያሕል እንደ ነገሠ የሚል ግመት አቅርቧል። በራይሆልት አሳብ ተከታዩ ሰኸተፒብሬ ነበረ።

ቀዳሚው
6 አመነምሃት
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1800-1798 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰኸተፒብሬ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)