ሴንቲኔላውያን
Appearance
ሴንቲኔላውያን የበንጋል ባህረስላጤ ውስጥ በስሜን ሴንቲኔል ደሴት ላይ ከሰው ልጅ ሥልጣኔ ሁሉ ውጭ የሚኖር ብሔር ነው። ደሴቱ ከሕንድ አንዳማን ደሴቶች መካከል ነው። ምናልባት 50-100 ኗሪዎች እንዳሉበት ይታስባል። አጫጭርና ጥቁር እንደ አንዳማን ኗሪዎችም የመሰሉ ሰዎች ናቸው።
ከውጭ አለም በሚጎብኙ ሰዎች ላይ ብዙ ጊዜ ጥቃት ጥለዋልና ስለዚህ ቋንቋቸው ወይም ባሕላቸው በተመለከተ ብዙ አይታወቅም። ሕንድ አገር ይግባኝ ማለት ጥላ በ1962 ዓም ይግባኝ የሚል ድንጋይ አስቀመጠችበት፤ ወደ ደሴቱ መጓዝ በይፋ ክልክል ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ኮኮነት ከተጓዦች በሰላም ተቀብለዋል። በእራቁታቸው እንደሚሄዱ፣ ፍላጻ፣ ጦር ካገኙት ብረት እንደሚስሩ፣ ታንኳ መሥራት እንደሚያውቁ ማወቅ ችለናል።
በ1998 ዓም በስኅተት የደረሱባቸውን ሁለት ሕንዳዊ አሣጥማጆችን ገደሉ። እንደገና በኅዳር ወር 2011 ዓም አንድ አሜሪካዊ ክርስቲያን ሰባኪ ጆን ቻው እነዚህ በአለማችን ስለ ኢየሱስ ወንጌል ምንም ያልሰሙ መጨረሻ ሕዝብ ይሆናሉ ብሎ ስላመነ ወደነሱ ወንጌልን ለመሰብክ ሲሄድ ሰማዕት ሆኖ ተገደለ።