ሸንኖንግ በንጻው ጂንግ
Appearance
ሸንኖንግ በንጻው ጂንግ (神農本草經) ስለ አትክልትና እርሻ በቻይንኛ የተጻፈ ጥንታዊ መጽሐፍ ነው። ከ2000 ዓክልበ. በፊት በኖረው አፈታሪካዊ ንጉሥ ሸንኖንግ እንደ ተጻፈ ይላል። የዛሬው ተመርማሪዎች ግን እንደሚያስቡ መጽሐፉ ከ300 ዓክልበ. እና ከ200 ዓ.ም. መካከል ባሉት ዘመናት ተቀነባበረ። ጽሑፉ አሁን ጠፍቷልና ይዘቱ በፍጹም አይታወቅም፤ የ365 አትክልት ጥቅም በሦስት ክፍሎች እንደ ገለጸ ይታወቃል።
መጀመርያው ክፍል 120 የማይጎዱ ጠቃሚ የሆኑ ዕጽዋት ይዘርዝራል። ከነዚህም ረይሽዕ ዕንጉዳይ፣ ጂንሠንግ (የሥር አይነት)፣ ኩርኩራ፣ ብርቱካን፣ ቀረፋ እና የቻይና እንስላል (Glycyrrhiza uralensis) ይጠቀሳሉ።
2ኛው ክፍል 120 ሊጎዱ የሚችሉ በጥንቃቄ የሚወሰዱ መድኃኒት አትክልት ይዘረዝራል። በዚሁ መደብ ዝንጅብል፣ Paeonia እና ኪያር ይገኛሉ።
በመጨረሻው ክፍል 125 ጉዳት የሚያምጡ አትክልት ይዘረዝራል። ለምሳሌ ሩባርብና ኮክ እንደዚህ ይመደባሉ።
- Jean-Baptiste Du Halde SJ (1735). "Description Géographique, Historique, Chronologique, Politique et Physique de l'Empire de la Chine et de la Tartarie chinoise" (በFrench). በSeptember 3 2010 የተወሰደ.
- Yang, Shou-zhong. The Divine Farmer's Materia Medica: A Translation of the Shen Nong Ben Cao Jing. USA, Blue Poppy Press, 2007 Google Books May. 2011