ሹ-ኢሊሹ
Appearance
ሹ-ኢሊሹ ከ1872 እስከ 1862 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር። ማዕረጉ በይፋ «የኡር፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ነበረ።
የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ልዩ ልዩ ቅጂዎች ሹ-ኢሊሹ ለ፲ ወይም ለ፳ ዓመታት እንደ ገዛ ሲሉን፣ ፲ የዓመት ስሞች ለእርሱ ተገኝተዋል። የዓመት ስሞቹ ሁሉ ለጣኦታቱ ጌጣጌጥ ወይም ሕንጻዎች ስለ መሥራቱ ናቸው እንጂ ምንም ዘመቻ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ አይዘግቡም።[1] በ፪ኛው ዓመት ግን የተማረከውን የጣኦት «ናና» ምስል ከአንሻን ወደ ኡር አንዳስመለሰው ይታውቃል። ልጁ ኢዲን-ዳጋን ተከተለው።
ቀዳሚው እሽቢ-ኤራ |
የኢሲንና የሱመር ንጉሥ 1872-1862 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኢዲን-ዳጋን |