ሼህ ሁሴን ጅብሪል
ሼህ ሁሴን ጅብሪል በወሎ አካባቢ በአፈታሪክ በስፋት የሚታወቁ ሼህ ናቸው። የተወለዱት በወሎ ክፍለ ሀገር በወረሄመኖ አውራጃ፣ በባዙራ ምክትል፣ በባሆች ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ እምበለ ሴዳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በ1811 ዓ.ም. ገደማ እንደነበርና 1908 ዓ.ም. በተወለዱ በ97 ዓመታቸው ማረፋቸው ይነገራል።[1]
ሼህ ሁሴን ጅብሪል መፍረድ የጀመሩት ገና በሰባት ዓመታቸው እንደነበርና የሚናገሩትም መሬት ጠብ የማይል እንደነበር ይነገርላቸዋል። አሐዱ ወይም ቢስሚላሂ ብለው ፍርድ የጀመሩት ደግሞ በአጼ ዮሐንስና መምሬ ግርማ በተባሉ ቄስ ነበር ይባላል። የሗላ ሗላ ግን ወደፊት የሚሆነውንና የሚመጣውን ከነመፍትሔው ጭምር በግጥም ይተነብዩ እንደነበርና በዚህም ምክንያት ነገሥታቱም፣ መሳፍንቱም፣ ትንሹም ትልቁም ሳቸውን መጀን ማለት እንደጀመሩ ይነገራል። ምንም እንኳን በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ያካተትኳቸዉ ግጥሞች የሼህ ሁሴን ጅብሪል የራሳቸው ትንቢቶች ይሁኑ አይሁኑ የራሱ የሆነ ጥናትና ምርምር የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢሆንም፣ ሼህ ሁሴን ጅብሪል ግን በትንቢታዊ ግጥሞቻቸዉ ከአጼ ዮሐንስ አራተኛ ጀምሮ እስከ ወታደራዊ ደርግ አገዛዝ መጨረሻ፥ ምናልባትም አሁን እስካለንበት ኢሕአዴግ ዘመን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ታሪክ ቀድመው እንደተነበዩና በግጥም እንዳስቀመጡ በአፈታሪከ ይነገርላቸዋል። [2]
ከአጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሐንስ፥ አጼ ምኒልክ፥ እቴጌ ጣይቱ፥ ልጅ ኢያሱ፥ ንግሥት ዘውዲቱ፥ ተፈሪ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ደርግ፣ ወዘተ ጋር የተያያዙ ብዙ በርካታ ጉዳዮችም
4. https://zelalemkibret.files.wordpress.com/2011/03/gelaye4.pdf
- ^ "Archive copy". Archived from the original on 2011-09-14. በ2012-02-15 የተወሰደ.
- ^ zelalemkibret.wordpress.com/page/3/