ቀጥተኛ መስመር

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ቀጥተኛ መስመር ማለት በሁለት ነጥቦች የሚያልፍ፣ ጉብጠት የሌለው መስመር ነው። ይህ መስመር በጥንቱ የሒሳብ ሰው ዩክሊድ አጥብቆ የተጠናና፣ ለዩክሊዳዊ ጆሜትሪ እንደመሰረት ያገለገለ ጽንሰ ሐሳብ ነው። ዩክሊድ፣ መስመር ማለት ከእርዝመት በቀር ወርድም ሆነ ስፋት የሌለው ፣ በሁለት ነጥቦች መካከል የሚገኝ መስመር ብሎ ተርጉሞታል።

ከቀጥተኛ መስመር አንዱ ጸባይ፣ በሁለት ነጥቦች መካከል ሊሳሉ ከሚችሉ ማናቸውም መስመሮች ያነሰው አጭሩ መስመር ነው።

ከተፈጥሮ ኅግጋት አንጻር፣ ቁስ አካላት ፣ በተፈጥሮአቸው፣ ያለውጭ ጉልበት ተጽዕኖ፣ በተጓዙ ጊዜ ግዑዝነትዓቸው በቀጥታ መስመር እንዲጓዙ ግድ ይላቸዋል።

እንዲሁም፣ የብርሃን ጨረር በኦና ውስጥ በተጓዘ ጊዜ በቀጥታ መስመር ነው።