ኦና
Appearance

ኦና ማለት ምንም አይነት ቁስ የሌለበት ኅዋ ነው። ስለሆነም በኦና ውስጥ ድምፅ መጓዝ አይችልም።
ጠፈር ውስጥ የሚገኘው ኅዋ ሙሉ ለሙሉ ኦና አይደለም ምክንያቱም አልፎ አልፎ ጥቃቅን የቁስ አካላት ይገኝበታልና። እዚህ ምድር ላይ ፓምፕ በመጠቀም ኦና ይሰራል። ይሄውም ከአንድ ነገር ውስጥ አየርን መጥጦ በማስወጣት ነው። ሆኖም ይሄም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ኦና መፍጠር አይችልም። እስካሁን በተደረሰበት የቴክኖሎጂ ችሎታ፣ 99.9999% ኦና ለመፍጠር ተችሏል።