ቅምቦ
Appearance
ቅምቦ ወይም ጦቢያ (Calotropis procera) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ቊጥቋጦ ወይም አነስተኛ ዛፍ፣ ወፍራም ልጥ፣ ታላቅ ቅጠል አለው።
በቆላ ከ1500m በታች ተራ ነው። በዚህም ውስጥ ደረቅ፣ አሸዋማ ፈሳሽ መውረጃ ይመርጣል።
ላስቲኩ ባጠቃላይ ለሰውም ሆነ ለከብት እንደ መርዝ ይቆጠራል። እንስሶች አይበሉትም። ሆኖም፣ ቅጠሉና ቅርንጫፎቹ በመሬት ላይ ለአንድ ሌሊት ቢደረቁ፣ ለከብት መኖ ጸጥ ይላል።
ላስቲኩ የልብ ሽባነት ያደርጋል። እንድ መድሃኒት ለቁምጥና ተጠቅሟል።
አረንጓዴ ቅጠሉ በአፍአዊ አምቅ ማበጥን ለመቀነስ ተጠቅሟል። ሥሩም እንደ ቶኒክ፣ ለአባላዘር በሽቶች[1] ወይም ለእባብ ነከስ[2] እንደሚረዳ ተብሏል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
- ^ እስክዳር አበበ - የደባርቅ ባህላዊ ሕክምና 2003 ዓም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ