Jump to content

ቆርኪ

ከውክፔዲያ

ለእንስሳ ዝርያ፣ ቆርኬ ይዩ።

ቆርኪኢትዮጵያ ህጻናት ከድንጋይና ከቆርኪ የሚጫወቱት ጨዋታ ነው። ቆርኪ ደግሞ የመጠጥ ጠርሙሶች የቆርቆሮ መክደኛ ነው። ይህ ጨዋታ ብዙን ጊዜ በልጆች የሚተገበረው በክረምት ወቅት ትምህርት ቤት ሲዘጋ ነው። ብዙ አይነት የቆርኪ ጨዋታወች አሉ።ከእነሱ ውስጥ ዲሞ፣ጉርጌ፣ዋንጫ ወዘተ. የሚጠቀሱ ሲሆን በአብዛኛው ሁሉም ቆርኪን በመደርደር ከቆርኪው በመራቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በመጣል ድንጋዩን አርቆ የጣለው/ጣለቸው የመጀመሪያ እድሉን ይወስድና የተደረደረውን ቆርኪ ለመምታት ይሞክራል። በመታቸው ቆርኪዎች ልክም ይሰበስባል ማለት ነው። ብዙ ቆርኪዎችን የሰበሰበ ወይም በልጆች ቋንቋ የበላ የጫዋታው አሸናፊ ይሆናል። የቆርኪ ጨዋታ ፉክክርን፣ እቅድ ማውጣትን፣ ስልት አወጣጥና አተገባበርን ለህጻናት ያስተምራል።