ቋንጣ

ከውክፔዲያ

ቋንጣ ብዙውን ጊዜ ከበሬ ስጋ ተዘልዝሎ በሚጥሚጣ እና በአረቄ ወይም በጨው ታሽቶ የሚዘጋጅ የምግብ አይነት ነው። ስጋው በድርቀት ምክንያት ዕርጥበት ስለሚወጣለት ብዙ ጊዜ ሳይበላሽ ስለሚቆይ በመንገደኞች የተወደደ ነው። አንደስንቅነትም ያገለግላል።