ቋንጣ ፍርፍር
Appearance
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከቋንጣን እንጀራፍርፍር ነው።
መጀመሪያ አንድ በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት በጥቂት ዘይት እናበስላለን፡፡ በመቀጠል አንድ የሾርባ ማንኪያ በርበሬ ጨምረን በደንብ እናበስለዋለን፡፡ በመቀጠል አንድ ትልቅ ቲማቲም በደቃቁ የተከተፈ ተጨምሮ ይበስላል፡፡ሁሉት ፍሬ በደቃቁ የተከተፈ ነጭ ሽንኩር እንጨምራለን፡፡ በደንብ ደርቆ የተዘጋጀውን ቋንጣ እንጨምርና ጥቂት ካበሰል በኋላ ሁለት የቡና ስኒ ውሃ በልኩ ጨምረን በለምለም እንጀራ አፈርፍረን ለገበታ እናቀርባለን፡፡
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |