Jump to content

በር:ሳይንስ/ምርጥ ጽሑፍ

ከውክፔዲያ

ብርሃን


ነጭ ብርሃን የሁሉ ቀለሞች ድምር ውጤት እንደሆነ
ነጭ ብርሃን የሁሉ ቀለሞች ድምር ውጤት እንደሆነ

ብርሃን ነገሮች በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው። የብርሃን ሞገድ ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል። ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያፈልቃል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ሬዲዮራዳር እና ታህታይ ቀይ ይገኙበታል። ታላላቅ ወንድሞቹ ቢባል፣ ላዕላይ ወይን ጠጅኤክስ ሬይጋማ ጨረር ይገኛሉ። እነዚህ የብርሃን ወንድሞች በተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም ፣ የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም። ሆኖም ግን አንድ አንድ እንስሳት እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ብርሃን ሳይሆን እንደ ሙቀት ሆኖ ይሰማል። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ። ንቦች በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላልይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ።

ብርሃን ሞገድ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሌሎቹ ጨረራዎች የሞገድና እኑስ ሁለትዮሽተፈጥሮን አዋህዶ የያዘ ነው። ስለዚህና ስለመሳስሉት መሰረታዊ የብርሃን ባህርያት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ሥነ ብርሃን (ኦፕቲክስ) በመባል ይታወቃል። የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ምርምር ዋና ክፍል ነው። የበለጠ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ...