በር:ሳይንስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search


ሳይንስ
ወደ   ሳይንስ   ክፍል   እንኳን   ደህና   መጡ!

Green DNA icon.svg             Creative-Tail-Animal-bee.svg           Creative-Tail-test tube.svg           Creative-Tail-microscope.svg


ሳይንስ ከተጨባጩ ዓለም በሥርዓት መረጃ የሚሰበስብ፤ ከተሰበሰበው መረጃ ተነስቶ ዕውቀት የሚገነባ እና በተመክሮ ተፈትነው ጸንተው ሊቆሙ የሚችሉ ትንቢቶችንና ማብራሪያዎችን የሚነዛ የዕውቀት ዓይነት ነው።

በፍልስፍና አስገዳጅ ዕውነት (የአምክንዮ ዕውነት) እና አጋጣሚ ዕውነት (ሐቅ) የተባሉ ሁለት ዓይነት ዕውነቶች አሉ። የሳይንስ ዕውቀቶች በአጋጣሚ ዕውነቶች (ሐቆች)ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይህም ሲባል ለሀቆች እንዲህ ሆኖ መገኘትና፣ እንደዚያ ሆኖ አለመገኘት አስገዳጅ አመክንዮ የለም። ለምሳሌ የሎሚ ቀለም ቢጫ ነው፣ ይህ ግን በአጋጣሚ የሆነ ኩነት እንጂ ሎሚ ጥቁር ቢሆን ኖሮ ምንም የአመክንዮ መጣረስ አይኖርም። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ሰው ያለምንም ችግር፣ በጥሩ አመክንዮ፣ ሎሚ ጥቁር ነው እሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። ድምዳሜው ስህተት መሆኑን በምንም ዓይነት በአመክንዮ ብቻ ማዎቅ አይቻልም ምክንያቱም የአመክንዮ መጣረስ ስለማይፈጥር። በአጠቃላይ፣ ሀቆች በአዕምሮ ፍልስፍና ብቻ ሊደረስባቸው አይቻልም።

ሳይንስ በአመክንዮ ብቻ ሳይሆን በተጨባጩ አለም ውስጥ በመሞከር፣ ከተሞክሮውም ዕውነትና ውሸቱ እየጠራና እየተመዘገበ በሂደት እየተሻሻለ የሚሄድ የዕውቀት አይነት ነው። ለዚህ ስራ እንዲያመች ዘመናዊው ሳይንስ የሳይንሳዊ ዘዴ ን ይጠቀማል።

ዘመናዊው ሳይንስ ፣ ሰፊ ዕውቀትን በመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ይህን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል ያለተወዳዳሪ የሰውን ልጅ ህይወት በማሻሻል ላይ ይገኛል። በሽተኞች መታከማቸው፣ የእርሻ ምርት መትረፍረፍ፣ የመገናኛ ብዙሃን መፈጠርና ማደግ፣ ወዘተ...እነዚህ ሁሉ የዚህን ዕውቅት ሥኬት የሚያሳዩ ናቸው።Newtons cradle animation book.gif


ትምህርተ ሳይንስ


ለዕለቱ የተመረጠ የሳይንስ ምስል


NASA-Apollo8-Dec24-Earthrise.jpg


ጨረቃ ላይ ለመውጣት ዕድል ካገኙት ጠፈር ተጓዦች አንዱ ቢል አንደርስ ካሜራውን ከጨረቃ
አድማስ ባሻገር ወደ መሬት በማለም በ1960 ዓ.ም. የቀረጸው ምስል ነው። ፎቶው እንደሚያሳየው፣
መሬትን ከሩቁ ለሚመለከት፣ ሰማያዊ ቀለም እንደምትይዝ እና ድቡልቡል ክብ እንደሆነች ለመረዳት አያዳግትም።
ከፎቶው ላይ የሚታየው ግራጫ ነገር የጨረቃ ምድር ነው።

ለዕለቱ የተመረጠ የሳይንስ ጽሑፍግስበት

Solar sys.jpg

ግስበት ማናቸውም ግዝፈት ያላቸው ቁስ ነገሮች እርስ በርሳቸው እንዲሳሳቡ የሚያደርጋቸው የተፈጥሮ ጉልበት ነው። በዕለት ተለት ኑሮ ግዝፈት ያላቸው ነገሮች በአየር ከመንሳፈፍ ይልቅ ከመሬት ጋር እንዲላተሙ የሚያደረጋቸው፣ በሌላ አነጋገር ለነገሮች ክብደት የሚሰጣቸው የጉልበት ዓይነት ነው። የመሬት ግስበት ወይም በተለምዶ የመሬት ስበት መሬት ሌላ ግዝፈት ያለውን ነገር፣ ሰዎችን ጨምሮ የምትስብበት የተፈጥሮ ጉልበቷ ነው። ጨረቃ ከመሬት በራ የማትጠፋው የመሬት ግስበት አንቆ ስለያዛት ነው። ሜርኩሪን፣ ቬነስን፣ ሌሎች የተቀሩትን ፈለኮችንፀሐይ ዙሪያ ጠፍሮ ከምህዋራቸው በረው እንዳይጠፉ የሚያደርጋቸው የፀሐይ ግስበት ነው። ከዋክብትንና ሌሎች ግዙፍ ቁሶችን በየረጨታቸው መድቦ አስተቃቅፎ የሚይዛቸው ይኽው መሰረታዊ ጉልበት ነው። ግስበት፣ ባጠቃላይ መልኩ ፣ በጥልቁ ጠፈር ውስጥ ተበትኖ የሚገኘውን ቁስ እንዲጓጉል ያደርጋል። ከዚህ አንጻር ለመሬት፣ ለተስፈንጣሪ ከዋክብት፣ ለ ፈለኮች (ፕላኔቶች) ፣ ለከዋክብት፣ ለረጨቶችና መሰል ግዙፍ አካላት ጓጉሎ መፈጠርና ቀጣይ ህልውና አስፈላጊና መሰረታዊ ነው ፤ አለበለዚያ የመጓጎልና አንድ ሁነው የመቀጠል እድል አይገጥማቸውም ነበርና። በውቅያኖሶች ለሚፈጠሩ ማዕበሎች፣ ለወንዞች መፍሰስ፣ ለአዳዲስ ከዋክብትና ፈለኮች ውስጣዊ ከፍተኛ ሙቀት እና ሌሎች ህልቁ መሳፍርት ክስተቶች ተጠያቂ ጉልበት ነው። የበለጠ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ...

የሳይንስ መደቦች

የሳይንስ መደብ ክፍሎችለመሳተፍ

አዲስ የሳይንስ ጽሑፍ ለማቅረብ እሚከተለው ሳጥን ውስጥ ርዕሱን ያስቀምጡ!


የሳይንስ ቅርንጫፎች


አጠቃላይ የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ሥነ ቅመማ (ኬሚስትሪ) ሕይወት ያላቸው ነገሮች ጥናት (ባዮሎጂ)
Nuvola apps bookcase.svg
Logo physics.svg
Gnome-applications-science.svg
DNA icon.svg
ሥነ ሕክምና ሥነ መሬት ሥነ ፈለክ ተግባራዊ ሳይንስ
Red Cross icon.svg
Earth core icon.png


Crystal Project konquest.png


Gcalctool.svg

ሳይንስ