መጠነ እንቅስቃሴ

ከውክፔዲያ

መጠነ እንቅስቃሴ ( ሞመንተም momentum) ማለት በቁስ አካላት ውስጥ ያለ የእንቅስቃሴ ብዛት ነው።

ለምሳሌ 3ኪሎግራም የሆነ ድንጋይ በ10ሜትር በሰከንድ ወደ ሰሜን ቢጓዝ፣ እያንዳንዱ ኪሎግራም የድንጋዩ ክፋይ በ10m/s ፍጥነት እንዳለ ለማየት አያዳግትም። ስለዚህ ድንጋዩ 10m/s+10m/s+10ms = 30m/s ወደ ሰሜን አጠቃላይ መጠነ እንቅስቃሴ ከkg አንጻር አለው ይባላል። 3ሺህ ግራም ስላለው፣ 3000X10m/s = 30ሺህ m/s ወደ ሰሜን መጠነ እንቅስቃሴ ከግራም አንጻር አለው ይባላል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግራም ቁስ በ10m/s ስለሚጓዝ።

ስለዚህ የአንድ ቁስ-አካል መጠነ እንቅስቃሴ፣ በዚያ አካል ውስጥ ያለው መጠነ ቁስ በያዘው ፍጥነት ልክ ሲባዛ ተብሎ ሊተረጎም ይቻላል። ይህ ሐሳብ ወደ ሒሳብ ተለውጦ ሲጻፍ እንዲህ ይመስላል፦

መጠነ እንቅስቅሴ

p - መጠነ-እንቅስቃሴን ይዎክላል (በእንግሊዝኛ momentum)
m  - መጠነ ቁስን  ይዎክላል (እንግሊዝኛ mass)
v - የቁሱ ክፍልፋዮች የሚጓዙበትን ፍጥነት ይዎክላል (እንግሊዝኛ velocity)።

መጠነ እንቅስቃሴ የቁስ አባሎቹ ፍጥነት ድምር ውጤት እንደመሆኑ፣ የቬክተር ዓይነት መጠን ነው። ማለትም ልኬትና አቅጣጫ አለው። መለኪያው ደግሞ kg.m/s ነው።

{{{2}}}


አንድ እራሱን የቻለ የቁስ ሥርዓት (ከውጭ ጉልበት የማያርፍበት)፣ በውስጡ ያለው መጠነ እንቅስቃሴ ምንጊዜም አንድ አይነት ነው። ይህም ሐቅ ኒውተን ሦስተኛ የ እንቅስቅሴ ሕግ ባለው መርሁ ያረጋገጠው የሳይንስ ጽንሰ ሐሳብ ነው። ስለዚህም በ10m/s የሚጓዝ 1ኪሎግራም ቁስና በ1m/s የሚጓዝ 10ኪሎግራም ቁስ፣ ሁለታቸውም እኩል መጠነ-እንቅስቃሴ አላቸው ይባላል፣ አንድ ዓይነት አቅጣጫ እስከያዙ ድረስ።