Jump to content

በር:ፍልስፍና/የተመረጠ ጽሑፍ/52

ከውክፔዲያ

ሥርዐት አንዱ የሌላ ጥገኛ የኾኑ ነገሮች ተሰብስበው የሚፈጥሩት ጥ ወይንም ምሉዕ ነገር ማለት ነው። አንድ ሥርዐት የቁስ አካላት ወይንም የሐሳብ/ሐሳቦች ወይንም የኹለቱም ስብስብ ሊኾን ይችላል።

ለምሳሌ አንድ ሰው በውስጡ ብዙ ሥርዐትን ይይዛል። ልብ፣ ሳምባ፣ እና የደም ቧምቧዎች ተደጋግፈው የአንድን ሰው የደም ሥርዐት ይፈጥራሉ። ጥርስ፣ ምላስ፣ ጨጓራ ...ወዘተ...እነዚህ ተደጋግፈው የምግብ ሥርዐትን ይፈጥራሉ። እያንዳንዱ ሥር ዐት በተራው አነሥተኛ ሥርዐቶችን ይይዛል። ልብ ከተለያዩ የደም ቧምቧዎች፣ ከስብ፣ ከጡንቻና ከኤሌክትሪክ የተሰራች ሥርዐት ናት። ከዚህ በታችም ቢዎረድ የበለጡ አነስተኛ ሥርዐቶች ይገኛሉ። ወደ ላይ ሲዎጣ፣ አንድ ሰው በራሱ የብዙ ሥርዐቶች ስብስብ የኾነ ሥርዐት ነው። ኹለትና ሦስት ሰዎች አንድ ላይ ሁነው የቤተሰብ ሥርዐት የፈጥራሉ። እንደዚህ እያለ ይኼድና እስከ ሀገርና ከዚያ በላይ የኾነ ሥር ዐት ይገኛል።.

ከሐሳብ አንጻር፣ ለምሳሌ ጂዎሜትሪእሙኖች እና እርጉጦች ስብስብ የኾነ የሒሳብ ሥርዐት ነው። ካልኩለስ እንዲሁ እራሱን የቻለ ሌላ የሒሳብ ሥር ዐት ነው።

የሐሳብና የቁስ ድብልቅ የኾነ ሥርዐት ቢባል ኮምፒዩተር እንደ ምሳሌ ሊዎሰድ ይችላል።

ነገሮችን በሥርዐት መረዳት እጅግ ጠቃሚ ከመሆኑ የተነሳ፣ በአኹኑ ዘመን ሥርዐቶች፣ በሒሳብ፣ በሳይንስ እንዲሁም በኢንጂነሪንግ በጥልቅ ይጠናሉ። መገልገያ ቁሶች ሲተለሙ፣ እንዲሁ ሥርዐት ባለው መንገድ መኾኑ ከፍተኛ ጥቅም አስገኝቷል። ለምሳሌ፣ መኪኖች ሲተለሙ፣ ኹሉም የመኪና አካላት በአንድ ጊዜ እና በአንድ ቡድን አይካኼድም። ይልቁኑ፣ አንድ ቡድን የመኪናውን የነዳጅ ሥርዐት ሲቀይስ፣ ሌላ፣ ስለ ነዳጅ እምብዛም የማያውቅ ቡድን ደግሞ የመኪናውን የኤሌክትሪክ ሥርዐት ዕቅድ ያዎጣል። ስለ ኤሌክትሪክም ኾነ ስለ ነዳጅ ምንም ዕውቀት የማያስፈልገው ሌላ ቡድን ደግሞ የመኪናውን የውጭ ክፍል ይዘይዳል። የመኪና ፍሬን ሥርዓት እራሱን በቻለ ቡድን ይተለማል። እነዚህ የተለያዩ ሥርዐቶች እንዲናበቡ ሲደረጉና አንድ ላይ ሲሰሩ፣ መኪና የተባለ ሥርዐትን ይፈጥራሉ። የዘመናዊ ሕንጻዎች አገነባብ፣ የ ዕጅ ስልኮች ወዘተ ... የሚመረቱትም በ እንደዚህ መልኩ ነው።