ብርጭቆ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
የፊንቄ ብርጭቆ ጋን፣ 1000 ዓክልበ. ግድም

ብርጭቆ ለመቅረጽ የሚችል፣ ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ውኁድ ሲሆን ብዙ ጥቅሞች አገኝቶዋል፤ ለምሳሌ መስኮት በመሥራት ይጠቀማል።

ብርጭቆ መጀመርያው በጥንት የተገኘው የሸምበቆ አመድ (አልካሊ) ከቀለጠ አሸዋ (ሲሊካ) ጋራ ሲቀላቀል ነበር። የብርጭቆ ኢንዱስትሪ የጀመረው ምናልባት 1900 ዓክልበ. በፊንቄ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድሞ በተመሳሳይ ዘዴ ሴራሚክ ወይም ሸካክላ በመሥራት በድንገት የተፈጠረ የብርጭቆ ዶቃ አለ።