ነጥሮን

ከውክፔዲያ
ነጥሮን ያለበት የግብጽ ሰማያዊ ሸክላ ማስቀመጫ

ነጥሮን በጥንት እንደ ሳሙና የጠቀመ ማዕድን ነው። የአምቦ አመድ ጨው አይነት ሲሆን ውሃ አዘል ሶዲየም ከሰላ ነው።

ነጥሮን በጥንት በተለይ በጥንታዊ ግብፅ ከደረቁት ሐይቆች ወለል ይወሰድ ነበር። ለልብስና ሰውነት ሳሙና ጥቅም ከዘይት ጋር ይቀላቀል ነበር። ከዚህ በላይ ለአፍ ማጠቢያ፣ ለፀረ-ሕዋስ መድኃኒት፣ አሣን ወይም ሥጋን ለመጠበቅ፣ ጠፍርን በመፋቅ፣ እንዲሁም ግብጻውያን ሬሳ እንዳይፈርስ ሲጠብቁ በተጠቀሙት መድኃኒት ውስጥ ነጥሮን ይጨመር ነበር። በሸክላም ሆነ በብርጭቆ ውስጥ ሲጨመር ደግሞ ሰማያዊ ቀለም ለመስጠት ነበር።

ቃሉ ነጥሮን፣ በዓረብኛ /ናጥሩን/፣ በግሪክኛም /ኒትሮን/፣ በአካድኛ /ኒትሩ/፣ በአራማይክ /ኒጥራ/፣ በዕብራይስጥ /ኔቴር/፣ በግብጽኛ /ነጨሪት/ ሆነ። «ነጨሪት» በግብጽኛ ደግሞ «የተነጠረ፤ የአምላክ» ማለት ሲሆን ከ

R8

/ነጨር/ ወይም «አምላክ» ነው። በአማርኛግዕዝ ቃሉ «ንጥር» በጥንተ ንጥርእድገንጥር እና ንጥር ቅቤ ደግሞ ከዚህ ጽንሰ ሐሣብ ጋር ይዛመዳል።