ብዕር

ከውክፔዲያ
Parker Duofold የሚባሉት ብዕሮች

ብዕር ጽሁፍን በጠፍጣፋ ወለል (ወረቀት) ላይ እንዲያርፍ የምንጠቀምበት ጫፉ ላይ ባለድቡልቡል ክፍተት ያለው እና በውስጡ ውሀን መሰረት ያደረገ ቀለም ያለው የጽህፈት መሳሪያ ነው። ይህ ቀለም ወደመጻፊያ ክፍተቱ የሚወርደው በዋነኛነት የመሬት ስበት እና የስርገትን ህግ በመጠበቅ ነው። ይህ አይነቱ የፅሕፈት መሳሪያ በአሁኑ ጊዜ በተለመደው እና በስፋት ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ባለው እስክርቢቶ ተተክቷል።