ቦሊውድ

ከውክፔዲያ

ቦሊዉድህንድ ሙምባይ ከተማ የሚገኘው የሃገሪቱ የፊልም ኢንዱስትሪ መጠሪያ ነው። ይህ መጠሪያ በስህተት የአጠቃላይ ህንድ ፊልሞችን እንደሚዎክል ይነገራል። ነገር ግን የሃገሪቱ ሲኒማ አንድ ክፍል ብቻ ሲሆን በሃገሪቱ ቁጥር አንድ በአለም ደግሞ ከትላልቅ የፊልም አዘጋጅ ቦታዎች አንዱ ነው።