ተልባ

ከውክፔዲያ
ተልባ

ተልባ (Linum usitatissimum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኢትዮጵያ ወይም በየትም አገር ተልባ ስለ ዘሩ ይታረሳል።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባጠቃላይ የሚያለዝብ የሚያስቀምጥ መጠጥ ሆኖ ይጠቀማል። ከሁዳዴ ጾም በኋላ ለፋሲካ ድግስ ለማዘጋጀት የሚያለዝብ ተልባ መጠጥ ይጠጣል። መጠጡም ለመስራት፣ ዘሮቹ ትንሽ ይጠበሱና ይፈጩ።

የቀቀለ ዘሩ መዳን ለማፋጠን በቁስል ላይ ይደረጋል። ይህ ዘዴ ደግሞ ጥይት ከቁስል ለማውጣት እንደሚረዳ ተጽፏል።[1]

ተልባ ወጥ ይሠራል። ከዘሩ ምግብ በላይ ስለ ዘይቱ እና ስለ ጭረቱ (ተልባ እግር) ይታረሳል። ተልባን መብላት ኮሌስትሮልን ከደም ለማጥራት፣ የደም ግፊትንም ለማሳነስ እንደሚችል በዘመናዊ ሳይንስ ታውቋል።

የደረቀ ተልባ ዘር መረቅ በስኳር ለትቅማጥ መስጠቱ ተዘግቧል።[2]

  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች