ቲፊናቅ

ከውክፔዲያ
«ቲፊናቕ» በሞሮኮ አዲስ ቲፊናቅ (ከነአናባቢዎቹ)

ቲፊናቅ (ቲፊናቕ) በስሜን አፍሪቃ የሚገኙት የበርበር (ኢማዚቐን) ብሔሮች የሚጠቅሙት አጻጻፍ ነው። ያለ አናባቢዎች የሆነ ቲፊናቕ በተለይ በማሊና በኒጄር የሚኖሩት ቷሬግ ሕዝብ ቋንቋቸውን ለመጻፍ ይጠቀማል። ከዚህ በላይ ባለፈው ቅርብ አመታት አናባቢዎች ጨምረው በሞሮኮ አዲስ ቲፊናቅ መደበኛ ሁኔታ አገኝቷል።

የ«ቲፊናቅ» ትርጉም «የፊንቄ ጽሕፈት» እንደ ሆነ ይታመናል። በጥንት በስሜን አፍሪቃ ከሠፈሩት ዘሮች መካከል የፊንቄ ወይም ከነዓን ሰዎች በተለይ በቀርታግና ዙሪያ እንደ ነበሩ ታውቋል። ፊንቄያውያንም የአልፋቤት አባቶች በመሆናቸው የስሜን አፍሪቃ ኗሪዎች ከነርሱ የተማሩበት ወቅት ግን አይታወቅም። የአሁን ሊቃውንት ከ500 ዓክልበ አስቀድሞ አይሆንም ሲሉ ለዚህ መልስ ማስረጃ የለም። የቲፊናቅ ጽሕፈት ከጥንታዊ የሊብያ በርበሮች ጽሕፈት ጋር ተመሳሳይነት ስላለው አደረጃጀቱ በዚህ ሊታይ ይችላል።

ፊንቄ ድምፅ ጥንታዊ ሊብያ ቲፊናቅ
Aleph
Beth Yab
Gimel Yag
Daleth Yad
He Yah
Waw Yaw
Zayin Yaz
Heth Yaḥ
Teth Yaṭ
Yodh Yay
Kaph Yak
Lamedh Yal
Mem Yam
Nun Yan
Samekh Yas
Ayin
Pe ፐ / ፈ Yaf
Sade Yaṣ
Qoph Yaq
Res Yar
Sin Yac
Taw Yat
Yat
Yaj

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቲፊናቅ በኦምኒግሎት]