ታላቁ እያሱ ግምብ

ከውክፔዲያ
ታላቁ እያሱ ግምብ፣ 1894ዓ.ም. (አንድ አንድ ክፍሎቹ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሳይፈርሱ)

ታላቁ እያሱ ግምብ (አድያም ሰገድ ግምብ)፣ በንጉሱ ታላቁ እያሱ ዘመን ተገንብቶ በ1677 (ዘመነ ማቲዎስ) የተጠናቀቀ ነበር። የአናጢዎች መሪ ወልደ ጊዮርጊስ ግምቡን የሰራው ሲሆን በጊዜው ከጠቢቡ ሰለሞን ቤት የብለጠ ያምር ነበር በመባል የተደነቀ ነበር። [1] የግምቡ ጣሪያ በወርቅና በከበሩ ደንጊያወች ያጌጠ ነበር። ወለሎቹም ከዝሆን ጥርስና ከቅጠላቅጥል ጌጦች የተሰራ ነበር።[2] ግምቡ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በእንግሊዝ የአውሮፕላን ቦምብ ድብድባ የተጎዳ ቢሆም አብዛኛው ክፍሉ ግን አሁን ድረስ ሳይፈርስ ይገኛል።

ታላቁ እያሱ የደብረ ብርሃን ሥላሴንና ሌሎች ፯ ቤተክርስቲያኖችን በመገንባት በተጨማሪ ይታወቃል።

የታላቁ እያሱ ግምብ

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Budge,( 1928) pp. 409
  2. ^ ሪቻርድ ፓንክኸርስት፣ The Ethiopians: a history፣ ገጽ 111