Jump to content

ትምህርት ለመሪካሬ

ከውክፔዲያ

ትምህርት ለመሪካሬመካከለኛ ግብጽኛ የተጻፈ ጽሑፍ ሲሆን በጥንታዊ ግብጽ ጨለማ ዘመን የነገሡት የሄራክሌውፖሊስ ፈርዖኖች (9ኛ-10ኛ ሥርወ መንግሥታት በማኔጦን አከፋፈል) የአገዛዝ ሰነድ ነው።

የፓፒሩስ መጀመርያ ስለ ተቀደደ፤ የሚናግረው ንጉሥ ስም ጠፍቷል፤ «ለልጁ መሪካሬ» ማንበብ ተችሎ የግብጽ ንጉሥ መሪካሬ ከአባቱ የተቀበለው ትምህርት እንደ ሆነ ይመስላል። ይህ የትኛው ፈርዖን እንደ ነበር ለማለት አስቸጋሪ ነው፤ ነገር ግን በይዘቱ የቀደሙት የሄራክሌውፖሊስ ፈርዖኖች ቀቲ (አቅቶይ) እና መሪብሬ ስሞች ይጠቀሳሉ።

«በደቡባዊ ክፍላገር ላይ ክፉ አታድርግ፤ ስለርሱ የተናገረውን የመኖሪያውን ትንቢት ታውቀዋለህና... እኔ ለጢኒስ ደቡብ ጠረፉን በታወር መለስኩት። ንጉሥ መሪብሬ ያላደረገውን አድርጌ ከተማውን እንደ ጐርፍ ማረክሁት።»
«የቀድሞ ንጉሥ አቅቶይ በትምህርት ያዋጀ፦ ለግፈኛው ዝም ማለት መሥዋዕቱን ያፈርሳል...»
(ለተጨማሪ ቀቲ (አቅቶይ)ን ይዩ።)