Jump to content

ኅዳር ፳

ከውክፔዲያ

ኅዳር ፳ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፭ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፯፻፸፬ ዓ.ም. በሊቨርፑልብሪታንያ ከተማ የተመዘገበ የአፍሪቃ ሰዎችን በግዳጅ ለአገልግሎት የሚሸጥ ድርጅት ንብረት የነበረችው “ዞንግ” የምትባለው መርከብ ከጫነቻቸው ሰዎች መቶ ሠላሳ ሦሥቱን አፍሪቃውያኖች መርከበኞቹ በሕይወት እያሉ ወደ ባሕር ጥለው ገደሏቸው። በአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ለባርነት የሚጫኑ የአፍሪቃ ዜጎች በአውሮፓ ሕግ ፊት እንደ ዕቃ ንብረት እንጂ እንደ ሰው ስለማይቆጠሩ፣ ይሄንን ታላቅ ወንጀል የፈጸሙት ሰዎች አልተከሰሱም። የመርከቧ ባለቤቶች ግን “ለጠፋው ንብረት’’ የዋስትና ውል የሰጣቸውን ድርጅት በፍርድ ቤት የኪሳራቸውን ዋጋ እንዲከፍላቸው ክስ አቀረቡ።

፲፰፻፳፫ ዓ.ም. በፖሎኝሩሲያን በላይነት እና አስተዳደር በመቃወም የ”ትጥቅ ትግል” ተጀመረ።

፲፱፻፵ ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፍልስጥኤምን በሐይማኖት መሠረት ለሁለት ከፍሎ አንደኛው የይሁዳዊ መንግሥት፤ ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ የአረብ መንግሥት እንዲመሠረት የሚያስችለውን “ውሳኔ ፻፹፩” አጸደቀ። ይሄው ውሳኔ በድምጽ ሠላሣ ሦስት አገሮች ሲደግፉት፤ አሥራ ሦሥት አገሮች ተቃውመው አሥር አገሮች ደግሞ የድጋፍም የቅራኔም ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ ከነኝህ ከአሥር አገሮች መሀል ይገኛሉ።[1]


፲፰፻፹፰ ዓ.ም. ላይቤሪያን ከ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. እስከ ሞታቸው ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. በፕሬዚደንትነት የመሩት ዊሊያም ቫካናራት ሻድራክ ተብማን ተወለዱ። ፕሬዚደንት ተብማን የ”ዘመናዊቷ ላይቤሪያ” አባት በመባል ይታወቃሉ።

፲፯፻፸፫ ዓ.ም. በአውስትሮ-ሁንጋሪያ ግዛት የሁንጋሪያ እና የቦሄሚያ ንግሥት ማሪያ ጠሬዛ ሞተች።

  1. ^ http://en.wikisource.org/wiki/United_Nations_General_Assembly_Resolution_181