Jump to content

ነህሲ

ከውክፔዲያ

==

ነህሲ አሰህሬ
የ«አሰህሬ» ሐውልት
የ«አሰህሬ» ሐውልት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1753 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሸሺ መዓይብሬ
ተከታይ ኑያ
ሥርወ-መንግሥት 14ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ሸሺ መዓይብሬ ?

==


ነህሲ አሰህሬ ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1753 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ነህሲ ለአጭር ዘመን (ምናልባት ፮ ወር ያህል ብቻ) ፈርዖን ሲሆን፣ ሕልውናው ከበርካታ ቅርሶች ታውቋል። ፈርዖን ከመሆኑ በፊት «የፈርዖን በኩር ልጅ» ተባለ። በአቶ ኪም ራይሆልት አሳብ አባቱና ቀዳሚው ሸሺ መዓይብሬ ነበር፤ ንግሥቱም ታቲ የኩሽ መንግሥት ልዕልት ስትሆን የልጃቸው «ነህሲ» ስም ወይም መጠሪያ በግብጽኛ «ኩሻዊ» ማለት ነው።

ቶሪኖ ቀኖና ላይ ከሥርወ መንግሥቱ መጀመርያው የሚጠቀስ ቢሆን ከርሱ በፊት ስንት ቀዳሚዎች ከሰነዱ እንደ ጠፉ አይታወቅም። በራይሆልት ዘንድ ፭ ቀዳሚዎች ነበሩት። ከነህሲ በኋላ በዝርዝሩ ላይ ሃያ ያህል የፈርዖን ስሞች አሉ፤ እነዚህ ሁሉ ለአጭር ወራት የገዙ ይባላሉ። ከነዚህ ሁሉ ከ፪ ስሞች በሰተቀር አንዳችም የሚያረጋገጥ ቅርስ የላቸውም፤ ቅርስም የተገኘላቸው «መርጀፋሬ»፣ «ሰኸፐረንሬ» ብቻ ናቸው። በተጨማሪ የሚከተሉት ፈርዖኖች በቶሪኖ ዝርዝር ባይጠቀሱም ከጥቂት ቅርሶች (ጥንዚዞች) በዚህ ዘመን ያሕል እንደ ገዙ ታውቋል፦ ኑያ፣ ሽነህ፣ ሽንሽክ፣ ዋዛድ፣ ኻሙሬ፣ ያዕቆብ-ሃር። የዋዛድም መታወቂያ ምናልባት ከ«መርጀፋሬ» ጋር ሊስማማ እንደተቻለ ራይሆልት ያስባል። እነዚህ ነገሥታት ሁሉ በጣም አጭር ጊዜ ስለ ገዙ በቶሎ ሰለ ተተኩ የጌሤም አለቆች ኃይል ቶሎ ደከመ ማለት ነው። ከያዕቆብ-ሃር ዘመን በኋላ የጌሤም ኗሪዎች የራሳቸውን ፈርዖን እንዳልተፈቀዱ ይመስላል።

ቀዳሚው
ሸሺ መዓይብሬ
አባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን ተከታይ
ኑያ