ዋዛድ
Appearance
==
ዋዛድ | |
---|---|
የዋዛድ ጥንዚዛ ምልክት | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1746-1742 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሸንሸክ ? |
ተከታይ | ያዕቆብ-ሃር |
ሥርወ-መንግሥት | 14ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ዋዛድ ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1746-42 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ዋዛድ በነገስታት ዝርዝሮች አልተዘረዘረም። የሚታወቀው ከ፭ ጥንዚዞች ነው። ሌላው ስም («የሆሩስ ስም») አይታወቅም።
በመምህር ኪም ራይሆልት አሳብ፣ በቶሪኖ ቀኖና ላይ ከነህሲ በኋላ ለተገኙት ስሞች አንድ ቅርስ ለ«መርጀፋሬ» ብቻ ሕልውናውን ስለሚያስረዳ፣ የዋዛድ መታወቂያ ከመርጀፋሬ ጋራ ሊሆን ይችላል። ይህም ቅርስ አንድ ጽላት ነው። በዝርዝሩ ዘንድ «መርጀፈሬ» 3-4 አመታት ነገሠ፤ ከሌሎቹም ይልቅ ለረዘመ ጊዜ ቀረ።
ቀዳሚው ሸንሸክ |
የአባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን | ተከታይ ያዕቆብ-ሃር |