ነብካውሬ ቀቲ

ከውክፔዲያ
የነብካውሬ ቀቲ ካርቱሽ ያለበት የክብደት ድንጋይ

ነብካውሬ ቀቲመጀመርያው ጨለማ ዘመን (9ኛው ወይም 10ኛው ሥርወ መንግሥት) በግብጽ (ከሄራክሌውፖሊስ) የገዛ ፈርዖን ነበረ።

የነብካውሬ ኅልውና ከሁለት ምንጮች ብቻ ይታወቃል። አንዱ ቅርስ ስሙ የተቀረጸበት የሚዛን ክብደት ሲሆን ሌላው ደግሞ «ልዝቡ ገበሬ» በተባለው ሥነ ጽሑፍ ስሙ ሲጠቀስ ነው።[1] ማዕረጉ «የላይኛና ታችኛ ግብጽ ንጉሥ» ሲሆን መቼ እንደ ገዛ ግን በትክክል አይታወቅም። በአንዳንድ መምህር አስተሳሠብ ይህ ነብካውሬ ቀቲ የመሪካሬ ትምህርት ደራሲ ሊሆን ይችላል፣ ማስረጃ ግን የለም።

  1. ^ ስለ ነብካውሬ ቀቲ (እንግሊዝኛ)
ቀዳሚው
?
ግብፅ ፈርዖን
2200-2167 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰነን-...?