ናርቦን
Appearance
ናርቦን (ወይም ሃርቦን) በፈረንሣይ አፈ ታሪክ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ንጉሥ ነበረ። የጋላጤስ ልጅና ተከታይ ይባላል።
እርሱ የናርቦን፣ ፈረንሳይ ከተማ መሥራች እንደ ነበር የሚል ትውፊት አለ። ሮማውያን ይህን ከተማ ናርቦ ማርቲውስ ሲሉት ደቡብ ፈረንሳይ ከዚህ ከተማ ናርቦነንሲስ ክልል አሉት።
ምንጮች ስንት ዓመት እንደ ገዛ በማወራት ይለያያሉ፤ ለ፲፰፣ ፳፣ ፳፪ ወይም ፴ ዓመታት መሆኑ የሚሉ መጻሕፍት ይገኛል። ንጉሥ ናርቦን በልጁ ሉግዱስ ተከተለ።
በአንድ ታሪክ ዘንድ ናርቦን ይህንን ሕግ አወጣ፦ «ዝሙት የተፈረደባት ሚስት ንብረቷን ራሷንም ስንኳ ታጣለች፤ የባሏን ባርያ ትሁን፤ ለአንድ ሰዓትም በራቁቷ ሩጣ። የዝሙት ጓደኛዋ ወንዱ ለዚያም ጊዜ ያህል ይሩጥና በበትሮች ይመታ። ወንድና ሴት ሁለቱ አንድላይ በራቁታችው ቢገኙ፣ ወይም የወንዱ ሱሪ ከተፈታ፣ የዝሙት ክስ ነው፤ ድምፅም ከተሰማ ይፈረድባቸዋል።»
በዚሁ ድንጋጌ ግን የሀገሩ ሴቶች እጅግ ተናድደው አንድ ቀን ከማደን ሲመልስ ድንጋዮች በመወርወር ገደሉት። ስለዚህ ተረቱ «ንጉሥ ናርቦንን አስታውስ» ሆነ።[1]
ቀዳሚው ጋላጤስ |
የኬልቲካ / ጋሊያ ንጉሥ 1909-1879 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ ሉግዱስ |
- ^ Histoire ancienne et moderne des départemens belgiques 1806 እ.ኤ.አ. (ፈረንሳይኛ)