ኖዕል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የኮርያ ባህላዊ ዩት ጨወታ ሠንጠረዥ

ኖዕል (ኮሪይኛ፦ 노을) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን አሱል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።

በጠቅላላ ለ59 ዓመታት (ምናልባት 1735-1676 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ዶሄ ተከተለው።

1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ኖዕል ካደረጋቸው ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦

  • 1734 ዓክልበ. ግ. - አውሬዎች መጀመርያ ከለማዳ እንስሶች ጋራ ወደ በረት ተጨመሩ።
  • 1733 ዓክልበ. ግ. - ዳንጉን እራሱ የሕዝቡን ኑሮ ለመመርመር ጉዞ አደረገ፤ ስለ አኗኗራቸውም ጠየቃቸው። ንጉሣዊ ጋሪ ከቤተ መንግሥት ውጭ በቆመ ጊዜ ብዙ ጠቢባን ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።
  • 1730 ዓክልበ. ግ. - ትክክለኛ ያልሆኑትን ኹኔታዎች ለመፍታት ከቤተ መንግሥት ውጭ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተመሠረተ። ስለዚህ ከቤተ መንግሥት ሩቅ የኖሩት ሕዝብ ተደሰቱ።
  • 1719 ዓክልበ. ግ. - ከቤተ መንግሥት ምሥራቅ መግቢያ ፲ (፬ ኪሎሜትር ያህል) አንድ ቡሻይ በምድር አበበ፣ አልጠወለግምና ድንጋዮች አቆሙበት። በሰማያዊ ወንዝ፣ የዩት ጨወታ ሠንተረዥ ትርዒት የሸከመ ኤሊ መንፈስ አለፈ። ፸ ዕንቅብ ወርቅ በባልሄ ባህር ዳር ዙሪያ ተገኘ።
  • 1700 ዓክልበ. ግ. - የሕዝቡን ኑሮ ለመመርመር የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተመሠረተ።
  • 1676 ዓክልበ. ግ. - ዳንጉን ኖዕል ዓረፈና አልጋ ወራሹ ልዑል ዶሄ ዳንጉን ሆኖ ነገሠ።
ቀዳሚው
አሱል
ጆሰን ዳንጉን
1735-1676 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዶሄ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]