ጎጆሰን
Appearance
ጎጆሰን (고조선) የጥንታዊ ኮርያ መንግሥት ነበረ። ግዛቱ በተለይ በዛሬው ስሜን ኮርያና ለዛ ቅርብ የሆነው የቻይና ክፍሎች ይጠቀለል ነበር። እስከ 116 ዓክልበ. ድረስ ቆይጦ ነበር። ዋና ከተማው አሳዳል ምናልባት የአሁኑ ፕዮንግያንግ፥ ወይም ሓርቢን በማንቹርያ ነበር። ይህ ለኮርያ የነሐስ ዘመን ነበር፣ መሣርያቸው ሁሉ ከነሐስ የተሰሩ ነበር።
በመጀመርያው ንጉሡ ዳንጉን ዋንገም እንደ ተመሠረተ ይታመናል። የዚህ መንግሥት ስም «ጆሰን» ሲሆን፣ በኋላ ዘመን (ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) ሌላ «ጆሰን» የተባለ መንግሥት ስለ ኖረ፣ ዳንጉን የመሠረተው መንግሥት አሁን «ጥንታዊ ጆሰን» ወይም «ጎጆሰን» በመባል ይታወቃል። የፔዳል ወይም ሺንሺ መንግሥት ከ«ድብ» ወገንና «ነብር» ወገን ጋራ በማዋሀድ የጎጆሰንን መንግሥት አቆመ። ይህ በቻይና ንጉሥ ያው ዘመን እንደ ሆነ በልማዳዊ አቆጣጠር 2341 ዓክልበ. ሲሆን፣ በዘመናዊ ግመት በ2108 ዓክልበ. ግድም ይሆናል። በስሜን ኮርያ መምህሮች አስተሳሰብ ደግሞ ይህ በ2900 ዓክልበ ሆነ።