Jump to content

አሌክሳንድርያ፣ ቨርጂኒያ

ከውክፔዲያ

አሌክሳንድርያሰሜን አሜሪካቨርጂኒያ ስቴት ውስጥ የሚገኝ ከተማ ሲሆን፣ ከአገሪቱ ዋና ከተማ ከዋሺንግተን ዲሲ በ፮ ማይል ዕርቀት ላይ ይገኛል። ምንም እንኳ በፊቱ ዘመን አሌክሳንድርያ የካውንቲ ስፋት የነበረው ቢሆንም፣ በ፩፱፻፳ዎቹ ከቆዳ ስፋቱ ተከፍሎ የአርሊንግትን ካውንቲ ሲመሰረት፣ ከካውንቲነት ወደ ከተማነት ዝቅ ብሏል። ከዚህ በተረፈ፣ በፌርፋክስ ካውንቲ ውስጥ የሚገኝ አሌክሳንድሪያ ተብሎ የሚታወቅ ክፍል ቢኖርም፣ ይህ ግን የፌርፋክስ አካል እንጂ የአሌክሳንድርያ ክፍል ተብሎ አይቆጠርም።

አሌክሳድንርያ በአሁኑ ወቅት ከ151,218 በላይ ህዝብ ይኖርበታል። የከተማው ዋና ማዕከል 'ኦልድ ታውን' ተብሎ ሲታዎቅ ለፖቶማክ ወንዝ በጣም የቀረበ ነው።