Jump to content

አማኑኤል ካንት

ከውክፔዲያ
ኢማኑኤል ካንት (1724 - 1804)

አማኑኤል ካንት ( Immanuel Kant) ከ(1724-1804) የነበረ ጀርመናዊ ፈላስፋ ሲሆን በምስራቃዊ ፕሩሲያኮይንበርግ ከተማ ተወልዶ፣ ከዕለተ ውልደቱ እስከ እለት ሞቱ ከኮይንበርግ 50 ማልይ በላይ ሳይሄድ በዛች በትወሰነች ከተማ ኑሮውን መርቷል። ካንት በርግጥ ውጫዊ ህይወቱ ብዙ ለውጥ ያልታየበት ቢሆንም፣ በአስትሳሰብ ግን የዘመኑን ፍልስፍና ከስር-መሰረቱ ቀይሯል። "ቀኝ" እና "ግራ" በኅዋ ውስጥ እንዴት ሊለዩ ይችላሉ የሚለውን ጽሁፍ በ1770 ለዶክትሬቱ መመረቂያ ካቀረበ ጀምሮ ለዘመናዊ ፍልስፍና ያለመታከት ብዙ ጽሁፎችን አቅርቧል። በነዚህ ጽሁፎች ውስጥ የካንት መሪ ሃሳብ "ማንኛውም የሰው ልጅ እውቀት ከበስተጀርባው የሰው ልጅን አእምሮ በተነሳሽ (active) ተሳታፊነት ያጠይቃል" የሚል ሲሆን፣ በርግጥ ይህ አስተሳሰብ ቀላል መስሎ ቢታይም ውስጡ ግን ብዙ ከባድና የተወሳሰቡ ጽንሰ ሃሳቦችን በመያዙ ከሱ በኋላ ለተነሱ ፈላስፋወች የሃሳብ ውቅያኖስ በመሆን እስካሁን ዘመን ድረስ በሱ ስራ ላይ ጥናት ይካሄዳል።

ትችት በአምክንዮ ላይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1781 እና በ1787 ባሳተመው የንጹህ አምክንዮ ትችት (ጀርመንኛ፡ Kritik der reinen Vernunft) መጽሃፉ ላይ፣ የሂሳብሳይንስ እና ስነ ውን እውነታወችን ለመገንዘብ የሚያስፈልጉን ቅድመ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ባማንሳት የተሟላ መልስ ለመስጠት ሞክሯል። ካንት የሰውን ልጅ ግንዛቤ በሁለት ከፍሏል፣ እነሱም ቀዳሚ (ማለት ከተሞክሮ ውጭ የሚታወቅ እውነት (a priori or analytic)) እና ተከታይ(ፍልስፍና) (ማለት ከተሞክሮ በኋላ የሚገኝ እውቀት (a posteriori)) ናቸው። ነገር ግን ካንት ከሁሉ ሁሉ ትኩርት የሚስቡና በርግጥም በጣም ጠቃሚ ዕውቀት ናቸው ያላቸው ተከታይ(ፍልስፍና) ቀዳማዊ ግንዛቤ ናቸው ያላቸውን ነው። እነዚህም እውነታወችን ለመገንዝብ በርግጥ የሰው አዕምሮ በምን አይነት ሁኔት እንዳለ እራሱን ማወቅ ይኖርበታል ይላል ካንት።

ከዚህ በመነሳት በሂሳብም ሆነ በሳይንስም ሆነ በለት ተለት ህይወታችን ውስጥ ቁስ አካሎች በኅዋ እና ጊዜ ውስጥ ተንጣለው እንድሆኑ አድርገን የምንገነዘብበት ምክንያት አእምሯችን እራሱ ጊዜንና ኅዋን በማፍለቅ ቁስ አካላትን በዚህ እራሱ ባፈለቀው ሁለት ጽንሰ ሃሳቦች ስለሚደረድራቸው ነው ይላል። በሳይንስም በኩል ማናቸውንም ተመክሮ በ መንስዔ እና ክትለት (cause and effect) ሰንሰለት አያይዞ የሚያስገነዝበን አዕምሯችን ነው። ግን እነዚህ አይነት መሪ ሃሳቦች የሚሰሩት ለምናውቀው የተሞክሮው አለም እንጂ ሥነ መልኮት እና ሥነ ውን (metaphysics) በሚያጠኑት ከተሞክሮ ውጭ ለሆነው ለሌላው አለም አይሰራም።

ግብረ ገብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

<<ካንት>> ከዚህ በተጨማሪ የግብረ ገብ ፈላስፋ ነበረ። ስለሆነም በ1785 (ጀርመን፡ Grundlegung zur Metaphysik der Sitten) የግብረገብ መሰረት ሥነ ውን የሚለውን መጽሃፉን ለህትመት አቅርቧል። .በዚህ ትንተናው ለሁሉም የሰው ልጅ የሚሰራ ብሎ ያመነበትን ዓለም አቀፍ ግብረገብ አበርክቷል። እኒህን የግብረገብ ህጎች የሁልጊዜ ግዴታ በማለት ተንትኗል። ይህ የሁልጊዜ ግዴታ ሲብራራ እንዲህ ይላል፡ አንድ ነገር ስትፈጽም (ስታደርግ) ያ ያደረከው ስራ ዓለም አቀፋዊ ህግ እንዲሆን በመፍቀድ ይሁን [1]ይላል። ለምሳሌ፡ ዛሬ ብትሰርቅ፣ መስረቅ ላንድ ጊዜ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን ለሁሉል ብሁሉም እንዲፈቀድ ፈቃድህ ይሁን፣ አለበለዚያ አትስረቅ ማለት ነው። ወይም ደግሞ እውነት ለመናገር ከወሰንክ፣ ላንድ ጊዜ ብቻና ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ሰው በሁሉ ቦታ እውነት እንዲናገሩ ፈቃድህ ነው ማለት ነው። በሌላ ቋንቋ፣ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ሰው፣ በሁሉ ጊዜ ፣ በሁሉ ቦታ እንዲደረግ የምትፈቅደውን ነገር ብቻ አድርግ። ካንተ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የእግዚአብሄርን መኖር፣ የነጻነትን መኖር፣ እና ዘላለማዊ ኑሮን እንደመነሻ በመውሰድ ነበር።

በቀሪው ዘመኑ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በቀሪው ዘመኑ፣ <<ካንት>>፣ ሳይንስና አርትን በማዋሃድ በአንድ አይን ሊመለከታቸው በቃ። (ጀርመን፡ Kritik der Urteilskraft (Critique of Judgment) (1790). ከዚያም ስለ ሃይማንቶ በ1793 ጽሁፍ አቅርቧል (ጀርመን፡ Die Religion innerhalb die Grenzen der blossen Vernunft (Religion within the Limits of Reason Alone))። ቀጥሎም <<መማር>> ማለት ምን ማለት ነው ለሚውለው ጥያቄ (ጀርመን፡ Beantwortung der Frage: Was ist Aufklärung? ("What is Enlightenment?" (1784)) መልስ ሲስጥ በስተመጨረሻ በ1795 አለም አቀፍ ትብብር በሁሉ አለም እንዲኖር ተማጽኗል (ጀርመን፡ in Zum ewigen Frieden (Perpetual Peace) )።

ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Kant, Immanuel; translated by James W. Ellington [1785] (1993). Grounding for the Metaphysics of Morals 3rd ed.. Hackett. pp. 30. ISBN 0-87220-166-x.