አርጌንቶማጉስ
Appearance
አርጌንቶማጉስ | |
---|---|
የሮማውያን ቴያትር ፍርስራሽ | |
ሥፍራ | |
መንግሥት | የሮሜ መንግሥት |
ዘመን | 50-400 ዓ.ም. ገደማ |
ዘመናዊ አገር | ፈረንሳይ |
ጥንታዊ አገር | ጋሊያ |
አርጌንቶማጉስ በሮሜ መንግሥት ዘመንና ከዚያም በፊት የጋሊያ (አሁን ፈረንሳይ አገር) ከተማ ነበር። ቢቱሪጌስ የተባለ ጎሣ በዙሪያው ይኖር ነበር። 42 ዓ.ም. አካባቢ ሮማውያን ያዙት። ፍርስራሹ ከዛሬው አርዠንቶን-ሱር-ክሮይዝ አጠገብ ይገኛል።
አርጌንቱም ማለት «ብር» ሲሆን የማጉስ ትርጉም «ገበያ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚያ ዘመን አያሌ ገበዮችና መንደሮቹ «-ማጉስ» በሚለው ስም ይጨረሱ ነበር። በአንድ ትውፊት ግን ማጉስ ከተሞቹን የመሠረተው የጥንት ንጉሥ ስም ነበረ።