Jump to content

ማጉስ

ከውክፔዲያ

ማጉስ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ሁለተኛ ንጉሥ ነበረ። የሳሞጤስ ልጅና ተከታይ ሲሆን ለ49 ዓመት (ምናልባት 2263-2214 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ ተብሏል። ዜና መዋዕሉም በጋሊያ ብዙ መንደሮች እንዳቆመ ይጨምራል።

በአሁኑ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝሆላንድ፣ ምዕራብ ጀርመንና ስሜን-ምዕራብ ጣልያን ብዙ ከተሞች በጥንት ስማቸው ላይ «-ማጉስ» የሚለውን መድረሻ ስለ ነበረ በዚህ ንጉስ ማጉስ እንደ ተመሰረቱ የሚሉ ደራስያን አሉ። ለምሳሌ፣ በፈረንሳይ ሩዋን (ሮቶማጉስ) እና በእንግሊዝ ቸስተር (ኒዮማጉስ) ከተሞች በማጉስ ተሠሩ ብለው ያምናሉ። ከነዚህ በላይ ብዙ ሌሎች ከተሞች ጥንታዊ ሮማይስጥ ስሞች በዚያ ዙሪያ በ -ማጉስ ጨረሱ። እንዲሁም፦

በፈረንሳይ፦

በእንግሊዝ፦

በምዕራብ ጀርመን (ከራይን ወንዝ ምዕራብ)፦

ሌሎች፦

ማጉስ እጅግ ጥበበኛ ስለ ነበር አንድ የጠቢቦች ክፍል ስለ ስሙ «ማጉስ» (ብዙ ቁጥር፦ ማጊ) ተነሥቶ እነኚህ ማጊዎች ትምህርታቸውን በፋርስ አገር ተስፋፉና ሰብአ ሰገል እንደ ሆኑ የሚሉ ጸሓፊዎች አሉ።

ቀዳሚው
ሳሞጤስ
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ
2263-2214 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሳሮን